ለወትሮ ሀሜት የማያጣው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ትኩረት ሊሰጠው ወደ ሚገባው ምዕራፍ ተሸጋግሯል።
የ2018 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በሁለት ምድብ ተከፍሎ በድምሩ ሀያ አንድ ክለቦችን እያሳለፈ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቀርተውታል። ወደ ሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚያድጉ ሁለት ክለቦችን ብቻ የምድብ መሪ መሆን ከቻሉ የሚለየው ይህ ውድድር ካለፉት ወራቶች በበለጠ ትኩረት ወደሚያስፈልገው የመጨረሻዎቹ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ተሸጋግሮ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ወደ ፕሪምየር ሊጉ የማደግ በለሱ ቀንቷቸው የነበሩ አንዳንድ ክለቦች ከሜዳ ላይ ውጤት ይልቅ ከጀርባ በሚሰሯቸው ገንዘብን ተገን ያደረጉ ሌብነቶችን በመጠቀም የማደጉን አማራጭ ሲጠቀሙ ስናስተውል የነበረ ሲሆን ከዚህ በፊት የሚሰሙ ሀሜቶችንም ሆነ በጉልህ ያየናቸውን አስነዋሪ ስራዎች እንዳይደገሙ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ጥብቅ የሆነውን ክትትል ማድረግ እንዳለበት ይሰማኛል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር የምድብ ሀ በጅማ የምድብ ለ ደግሞ በሀዋሳ እየተደረገ ሲሆን እኔም ጨዋታዎቹን ለመመልከት እና ውድድሩ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ በአካል በመገኘት ክትትል ለማድረግ ጥረትን አድርጌያለሁ። በጅማ እየተደረገ የሚገኘው የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ውድድር 10 ክለቦች እየተሳፉበት ሲገኝ ሦስት ቡድኖች ከሌሎቹ ክለቦች በይበልጥ የማደግ ዕድልን ይዘው ተቀምጠዋል። ሊጉን በአሰልጣኝ ማቲዮስ ለማ የሚመራው ጋሞ ጨንቻ በ30 ነጥቦች ምድቡን በበላይነት ሲመራው የአሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ (ድሬ) የመዲናይቱ ተወካይ የሆነው የካ ክፍለከተማ እና ባቱ ከተማ በዕኩል 28 ነጥቦች በጎል ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን ውድድሩም ሊጠናቀቅ የአምስት ጨዋታዎች መርሀግብር ብቻ ከፊቱ ተቀምጠው ይገኛሉ።
ምድቡ ዛሬ ሻሸመኔ ከ ነቀምቴ ጋር ባደረጉት የሳምንቱ ክንውን መጀመር የቻለ ሲሆን ነገ ሐሙስ መሪው ጋሞ ጨንቻ ከተከታዩ የካ ክፍለ ከተማ ጋር እንዲሁም አቃቂ ቃሊቲ ሦስተኛ ላይ ከተቀመጠው ባቱ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ እጅግ ከፍ ያለ ቦታ ስለ ሚኖረው ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። በሀዋሳ እየተደረገ የሚገኘው እና 11 ክለቦች የሚገኙበት የምድብ ለ ውድድር የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ደሴ ከተማ እና በበሽር አብደላ የሚመራው ሀላባ ከተማ በዕኩል 28 ነጥቦች በጎል ተበላልጠው መቀመጥ የቻሉ ሲሆን ስድስት ጨዋታዎች ብቻ በቀሩት ይህኛው ምድብ ደግሦ ዕርብ ደሴ ከ ንፋስ ስልክ ሀላባ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር የሚያከናውኗቸው ጨዋታዎች ይቀጥላሉ።
የምድብ የበላይ የሆኑ ሁለት ክለቦች ብቻ በሚያድጉበት የሀገሪቱ ሁለተኛው የሊግ ዕርከን በተገኘሁባቸው ሜዳዎች ላይ ዳኞች ሜዳ ላይ ጨዋታን በትኩረት ከመዳኘት ይልቅ የተሳሳተ የህግ ትርጓሜን ሲወስኑ ፣ በስታዲየሙ ውስጥ የሚሰሙ እግር ኳሱን የማያሳድግ የሙስና ወሬዎች ሲደመጡ በጆሮዬ መስማት የቻልኩኝ ሲሆን ከዚህ ቀደም ዳኛን በገንዘብ የመያዝ ፣ እንዲሁም ወደ ሊጉ የማደግ ዕድል ያላቸው ክለቦች ከተጋጣሚ ቡድን አሰልጣኝ እና ተጫዋዋች ጋር በድብቅ በመገናኘች በገንዘብ አሳምኖ ወደ ሜዳ እንዲገቡ የማድረግ እና ከኮሜቴ ጋር ሙድ ውስጥ በመግባት ውጤት እንዲለወጡ ሲደረጉ ከዚህ ቀደም የተሰማ ሲሆን ጥቂት ሳምንት ግን ወሳኝ ወደ መሆን የቀረበው ይህ የዘንድሮ ውድድር በገንዘብ ከመጨማለቁ በፊት የውድድሩ የበላይ የሆነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ልዩ ጥንቃቄን ማድረግ እንዳለበት ለመጠቆም እወዳለሁ።ቀደም ዳኛን በገንዘብ የመያዝ ፣ እንዲሁም ወደ ሊጉ የማደግ ዕድል ያላቸው ክለቦች ከተጋጣሚ ቡድን አሰልጣኝ እና ተጫዋዋች ጋር በድብቅ በመገናኘች በገንዘብ አሳምኖ ወደ ሜዳ እንዲገቡ የማድረግ እና ከኮሜቴ ጋር ሙድ ውስጥ በመግባት ውጤት እንዲለወጡ ሲደረጉ ከዚህ ቀደም የተሰማ ሲሆን ጥቂት ሳምንት ግን ወሳኝ ወደ መሆን የቀረበው ይህ የዘንድሮ ውድድር በገንዘብ ከመጨማለቁ በፊት የውድድሩ የበላይ የሆነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ልዩ ጥንቃቄን ማድረግ እንዳለበት ለመጠቆም እወዳለሁ።
አስተያየት ይስጡ