By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “የወጣው ዝርዝር ላይ የማይመለከተው ሰው ካለ ለመቀጣት ዝግጁ ነኝ” “እያወረስን ያለነው ዕዳ አይደለም” “የሲዳማ ቡና እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳይ አላለቀም” አቶ ባህሩ ጥላሁን (የኢ.እ.ፌ ዋና ስራ አስፈፃሚ)
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዋልያዎቹየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንዜናዎች

“የወጣው ዝርዝር ላይ የማይመለከተው ሰው ካለ ለመቀጣት ዝግጁ ነኝ” “እያወረስን ያለነው ዕዳ አይደለም” “የሲዳማ ቡና እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳይ አላለቀም” አቶ ባህሩ ጥላሁን (የኢ.እ.ፌ ዋና ስራ አስፈፃሚ)

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 7 months ago
Share
SHARE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ቅዳሜ በአሜሪካ ከዲሲ ዩናይትድ ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታን ያደርጋል።

በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እየተመራ ለጨዋታው ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ በነገው ዕለትም 31 የልዑካን አባላትን በመያዝ ወደ አሜሪካ ያቀናል።

የብሔራዊ ቡድኑን ዝግጅት እና ከጉዞው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተመለከተ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን በዋነኝነት ከቪዛ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሰፋ ያለ ገለፃ የሰጡ ሲሆን የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ለሚጓዙት የልዑክ ቡድን አባላት ቪዛ ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

- ማሰታውቂያ -

በአሰልጣኝ መሳይ ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች መካከል 15 የሚሆኑድ አዲስ ቪዛ የጠየቁ ነበሩ ያሉት አቶ ባህሩ ከነዛም መካከል ሰባቱ አግኝተው ስምንቱ ግን ሊያገኙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል።

ከአራት የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ሁለቱ ፤ ከስድስት የስራ አስፈፃሚ አባላት ሶስቱ ቪዛ ያገኙ ሲሆን ሶስት(የቡድኑ ዶክተር ፣ የቡድኑ የስነ ምግብ ባለሙያ እንዲሁም የሚዲያ ኦፊሰር) ሌሎች አባላትም ቪዛ ማሳደሳቸውን ገልፀዋል።

35 የልዑካን ቡድን አባላትን ይዘን ለመሄድ ነበር ስምምነታችን ያሉት አቶ ባህሩ 31 የልዑካን ቡድን አባላት ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ ብለዋል።

ምንም እንኳን ዋና ስራ አስፈፃሚው 31 አባላት ይጓዛሉ ቢሉም በሰጡት መረጃ 28 ግለሰቦች ሲሆኑ ቀሪ ሶስቱ እነማን እንደሆኑ አልገለፁም።

ይሄ ጨዋታ አንድ የወዳጅነት ጨዋታ ብቻ ተደርጎ መቆጠር የለበትም ያሉት አቶ ባህሩ ጥላሁን ለሶስት ዓመታት ያህል የተደረገ የቢዝነስ ስምምነት ሲሉ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል።

በዚህም ጨዋታውን ስለሚያደርግ ብቻ 25 ሺህ ዶላር ጨዋታውን ካሸነፈ ደግሞ 50 ሺህ ዶላር በድምሩ ያለምንም ወጪ እስከ 75 ሺህ ዶላር ገቢን ያገኛል ብለዋል።

በጉዞው ከተካተቱት መካከል በተለይም የስራ አስፈፃሚ አባላቱን አስመልክቶ አቶ ባህሩ ጥላሁን ተከታዩን ብለዋል።

“የስራ አስፈፃሚ አባላት ይሄዳሉ ? አዎ ይሄዳሉ። የሚሄዱት ግን ምን አይነት ፋይዳን ሊያመጡ ነው የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። እሱን ለመመለስ የማርኬቲንግ ስራዎችንም ይሰራሉ። ከዲሲ ዩናይትድ የተለያዩ አመራሮች ጋርም በቀጣይ በሀገር ውስጥ አካዳሚዎችን ከመክፈት ጋር ሀሳብ አላቸው። የራሳቸውን ቡድን ከመመስረት አኳያ ብዙ ሀሳብ አላቸው። የራሳቸውን የምልመላ ቡድን ከማቋቋም ጋር ብዙ ሀሳብ አላቸው። ስለዚህ የሚሄደው አካል ጨዋታ አድርጎ የሚመለስ የቡድን አባላትን ብቻ ሳይሆን እንደዚህ አይነት ስትራቴጂክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሊሰሩ የሚችሉ አመራሮች ወደ ስፍራው ይሄዳሉ።”

የሚሄዱት ትክክለኛ ቦታ ላይ ነው ሲሉ ያከሉት አቶ ባህሩ ጥላሁን የተጓዦች ስም ዝርዝር ይፋ መሆኑን የሀገር ሚስጥር የወጣ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

“እውነት ለመናገር ፣ ግልፅ ለመሆን እንጥራለን። ግልፀኛ ለመሆን እየጣርን እንደሆነ ነው የሚሰማኝ ለምሳሌ ሰሞኑን ይፋ የሆነው ደግሞ የሀገር ሚስጥር የወጣ ነው የሚመስለው ፤ የትኬት ቡኪንግ ዝርዝር። ማን ምን እነደሆነ ማስረዳት እችላለሁ።”

አቶ ባህሩ ጥላሁን አክለውም በወጣው ዝርዝር ላይ የማይመለከተው ሰው ካለ ለመቀጣት ዝግጁ ነኝ ሲሉ ተናግረዋል።

የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ተርሙን ለመጨረስ አንድ አመት ከአንድ ወር ያህል ይቀረዋል ፤ በቀጣይም አመትም ይህ ስራ አስፈፃሚ ቡድኑን ይዞ የሚጓዝ ይሆናል ብለዋል።

ፋይዳው በሚገባ ከግምት መግባት አለበት ሲሉም በማከል ለቀጣዩ አዲስ የስራ አስፈፃሚ እዳ አይደለም እየሰጠን ያለነው ሲሉ ተናግረዋል።

“አቶ ኢሳያስ ጅራ ወደ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመጡ 16 ሚልዮን ብር ዕዳ ነው የተቀበሉት ፤ የዛኛው የስራ አስፈፃሚ ነው ዕዳው ስለዚል እነሱጋር ይቅር አይደለም የተባለው። ተቋም ሁሌም ይኖራል ፤ ውስጡ ያሉ ሰዎች ግን ይቀያየራሉ።”

“እያወረስን ያለነው ዕዳ አይደለም የተሻለ ነገር ነው። ይሄ ወደ አሜሪካ የሚደረገው ጉዞ ትክክል አይደለም እንቀይረዋለን ማለት ይችላል የሚመለከተው አካል ማስቀጠልም ይችላል። እኛ ካደረግነው በላይም የተሻለ ስምምነት ማምጣት ይችላል። ለሀገር የሚጠቅም ለተጫዋቾች የሚጠቅም ነገር መስራት ይችላል።”

ከሲዳማ ቡና እና ያሬድ ባየል ጃር በተያያዘ አቶ ባህሩ ጥላሁን ይህንን ብለዋል።

“የሲዳማ ቡና እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳይ አላለቀም ፤ ካስ ሄዷል። ካስም ጉዳዩን እያየ እየመረመረ እኛም ምላሽ እየሰጠን ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ አይመለከተውም ልንል የምንችልበት ምክንያት የለም። ሁለተኛ የብሔራዊ ቡድን ግዴት እና የክለብ ግዴታ ይለያያል። እኛ የጠራነው ለብሔራዊ ቡድን ግዴታ ነው።”

በሊግ ካምፓኒው በኩል የፋይናንስ ደንብ ጥሰት ፈፅመዋል በተባሉ ተጫዋቾች እና ክለቦች ላይ የተጣለውን ቅጣት አስመልክቶ በነበረው መግለጫ ላይ የተቀጡት ተጫዋቾች ለብሔራዊ ቡድንም አይጫወቱም ተብሎ ስለመነሳተለ ለቀረበላቸው ጥያቄም እኛ(የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን) አላልንም ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ባህሩ አክለውም ፌዴሬሽኑ በቅርቡ በአንድ የራዲዮ ጣቢያ ላይ የራሱን ፕሮግራም ሊጀምር ስለመሆኑ ገልፀዋል።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article “ወደ አሜሪካ በምናደርገው ጉዞ ምንም ወጪ የለብንም” አቶ ባህሩ ጥላሁን (የኢ.እ.ፌ ዋና ስራ አስፈፃሚ)
Next Article ካፍ ለቻን የአፍሪካ ዋንጫ 3 ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎችን መረጠ *…. በላይቤሪያ ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን የሰጡት የኤ ላይሰንስ ስልጠና ተጠናቋል…..

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የዝውውር ዜናዎችኢትዮጵያ ቡናዜናዎችሀዲያ ሆሳዕና

ጫላ ተሽታ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል !

Ermias Misganaw By Ermias Misganaw 2 years ago
አትሌት ሙክታር እድሪስ ስለ ሀዋሳ ግማሽ ማራቶን ይናገራል
አዲሶቹ የዳኞች ኮሚቴ ተመረጡ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት 6ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል።
የዳኞች ኮሚቴ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔን እንደማይቀበል ገለፀ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?