በአሜሪካ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የወዳጅነት የሚያደርገው የዋልያዎቹ ስብስብ ሀገር ውስጥ ለሚያደርገው ዝግጅት ከሚያወጣው ወጪ ውጪ በሚጓዙበት ወቅት የአውሮፕላን እና አሜሪካ ከተጓዙ በኋላ ያሉ የተለያዩ ወጪዎቹን ዲሲ ዩናይትድ የሚሸፍን ይሆናል ።
በዛሬው እለት በጁፒተር ሆቴል የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን እና የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ መግለጫ ሰጥተዋል ።
አቶ ባህሩ ስለ አሜሪካው ጉዞ እና ፌዴሬሽኑ ስለሚያገኛቸው ጥቅማ ጥቅም የገለፁ ሲሆን ዋሊያዎቹ በስፍራው ስለተገኙ ብቻ 25 ሺህ ዶላር የሚያገኙ ሲሆን በተጨማሪም ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻሉ 50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ ይሄም ገቢ ኢትዮጵያ ከ ግብፅ ጋር ካደረገችበች ጨዋታ በኋላ የሚገባ ከፍተኛ ገቢ እንደሚሆን ገልፀዋል።
በነገው ዕለት ወደ አሜሪካ የሚያቀናው ልዑካን ቡድን ሀያ ተጨዋቾችን ጨምሮ በአጠቃላይ ሰላሳ አንድ አባላት እንደሚጓዙ ገልፀዋል።
- ማሰታውቂያ -
የዋሊያዎቹ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ስለምርጫው ምርጫውን ቀድምን ነበር ያደረግነው ሁሉም ተጨዋቾች በግላቸው ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለፁ ሲሆን የመጀመሪያ ዕቅድ ቢበላሽ ብዬ የያዝኳቸውን ተጨዋቾች ነው ወደ ሰብስቤ ያካተትኩት ብለዋል።
የዋልያዎቹን ጨዋታ ለመታደም ወደ 12 ሺህ የሚጠጋ ደጋፊ እስካሁን ቲኬት መቁረጡም የተገለፀ ሲሆን ጨዋታውም የፊታችን ቅዳሜ የሚደረግ ይሆናል።
ዋሊያዎቹ በጨዋታው በማክሮን ትጥቅ አምራች ድርጅት የተመረተውን አዲስ ማልያ በጨዋታው እንደሚጠቀሙ አቶ ባህሩ ጥላሁን ገልፀዋል።


