ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ለምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ
ኢትዮጵያ ከሱዳን ለምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ አሰሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊፋ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ወቅትን በመጠቀም ከሱዳን ብሄራዊ ቡድን ጋር መስከረም 13 እና መስከረም 16 አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ያከናውናል። ለዚህ ጨዋታ እንዲረዳም የብሔራዊ ቡድናችን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ 23 ተጫዋቾችን ጥሪ አድርገዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች በነገው ዕለት ሪፖርት በማድረግ በቦሌ ጁፒተር ሆቴል ተሰባስበው ልምምድ የሚጀምሩ ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች
ግብ ጠባቂዎች
በረከት አማረ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሰኢድ ሀብታሙ (አዳማ ከተማ)፣ ዳንኤል ተሾመ (ድሬደዋ ከተማ)
ተከላካዮች
አስራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሱሌማን ሃሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ረመዳን የሱፍ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ጊት ጋትኩት (ሲዳማ ቡና) ፣ አስቻለው ታመነ (ፋሲል ከነማ) ፣ ፍሬዘር ካሳ (ሀዲያ ሆሳእና)
አማካዮች
ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሽመልስ በቀለ (ኤል ጉውና/ግብፅ) ፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ) ፣ በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ) ፣ ታፈሰ ሰለሞን (ፋሲል ከነማ) ፣ መሱድ መሀመድ (አዳማ ከነማ) ፣ ከነአን ማርክነህ (መቻል)
አጥቂዎች
በረከት ደስታ (መቻል) ፣ ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከተማ) ፣ ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና) ፣ ቸርነት ጉግሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)