ለ2025 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች በአዳማ ከተማ በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቹን እንደማያገኝ ተረጋግጧል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የማሚሎዲ ሰንዳውንሱ አቡበከር ናስር እና የዜዱ አቤል ያለው ከጉዳታቸው ባለማገገማቸው ቡድኑን አይቀላቀሉም።
በተጨማሪም በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሲዳማ ቡናን የተቀላቀለው መስፍን ታፈሰ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ከስብስቡ ውጪ ሆኗል።
በተያያዘም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስደናቂ ጊዜን ያሳለፈው አዲስ ግደይ ብሔራዊ ቡድኑን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀርቦለታል።