By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “ታሪክ ሰርተን ማለፍ እንፈልጋለን” “ዋንጫውን ብናነሳ በህይወቴ በጣም ደስተኛ የምሆንበት ቀን ነው” “ትኩረት ያደረግነው በኢትዮጵያ ዋንጫ ላይ ነው” “ከኛ ጎን ይሁኑ ፤ እኛም አናሳፍራቸውም” መስፍን ታፈሰ
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችሲዳማ ቡናቃለመጠይቅየኢትዮጵያ ዋንጫ

“ታሪክ ሰርተን ማለፍ እንፈልጋለን” “ዋንጫውን ብናነሳ በህይወቴ በጣም ደስተኛ የምሆንበት ቀን ነው” “ትኩረት ያደረግነው በኢትዮጵያ ዋንጫ ላይ ነው” “ከኛ ጎን ይሁኑ ፤ እኛም አናሳፍራቸውም” መስፍን ታፈሰ

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 9 months ago
Share
SHARE

የ2017 ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ስታድየም ሲደረግ ሲዳማ ቡናን ከወላይታ ድቻ ያገናኛል።

ሲዳማ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በውድድሩ ፍፃሜ ተገኝቷል።

በሲዳማ ቡና የውድድሩ የዋንጫ ጉዞ ላይ ትልቅ ሚናን ከተወጡት ተጫዋቾች መካከል አንዱ መስፍን ታፈሰ ነው።

መስፍን ታፈሰ ስለ ሲዳማ ቡና የውድድር ዓመቱ የሊጉ እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ጉዞ እንዲሁም የነገውን ተጠባቂ የፍፃሜ ጨዋታ በተመለከተ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ ጋር ቆይታ አድርጓል።

- ማሰታውቂያ -

በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ዙር ጥሩ አልነበርንም የሚለው መስፍን በተለይም ከአሰልጣኝ ለውጡ በኋላ በቡድኑ ላይ በሜዳ ላይ የሚታይ ግልፅ ለውጥ አሳይቷል ብሏል።

ሲዳማ ቡና በኢትዮጵያ ዋንጫ ጉዞው ሶሎዳ አድዋ ፣ ስሁል ሽረ ፣ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም መቻልን በመርታት ለፍፃሜው ደርሷል።

በዚህ ጉዞ ላይ ከባዱ ጨዋታ ሶሎዳ አድዋን የገጠመንበት ነው የሚለው መስፍን ያ ጨዋታ ጭንቀት ነበረው በቀጣይም ጠንካራ ተጋጣሚዎችን ድል አድርገን ነው ለዚህ የደረስነው ይላል።

“በኢትዮጵያ ዋንጫ አሪፍ ጉዞ ነው ያደረግነው ፤ የከፍተኛ ሊግ(ሶሎዳ አድዋ) ቡድኖችም አግኝተን ነበረ። በደንብ ፈትነውናል ብዬ ነው የማስበው ፣ እነሱ በጣም ነው የፈተኑን። በነሱ ፈተና ነው ለሁሉም እጅ ያልሰጠነው እና ለፍፃሜው ጠንክረን የደረስነው።”

ሲዳማ ቡና በሁለተኛው ዙር ሶሎዳ አድዋን መግጠሙ የሚታወስ ሲሆን በጨዋታው 2 ለ 0 ሲመራ ቆይቶ በመጨረሻ 15 ደቂቃዎች ሁለት ግቦችን በማስተናገድ በመለያ ምት 5 ለ 3 አሸንፎ ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል።

ቡድኑ ከሶሎዳ አድዋው ጨዋታ ውጪ ያሉ ሶስቱን ጨዋታዎች ሀዋሳ ላይ ነበር ያደረገው ፤ ይህም በበርካታ ደጋፊዎች ፊት በመጫወታችን ተጠቃሚ አድርጎናል ብሏል መስፍን ታፈሰ።

“በደጋፊ ፊት ስትጫወት ምን ማድረግ እንዳለብህ ታውቃለህ። ደጋፊም ደግሞ ምን ጊዜም ያግዝሀል ይደግፍሀል። እና የነሱ መኖር ለኛ ጠቅሞናል ብዬ ነው የማስበው።”

አሊቶዎቹ ተከታታይ ስምንት የሊግ ጨዋታዎች ላይ ያለ ሽንፈት ከተጓዙ በኋላ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች በመቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ መድን ተሸንፈዋል።

ቡድኑ ከፍፃሜው ጨዋታ በፊት ተከታታይ ሽንፈቶች ማስተናገዱ ተፅዕኖ ያሳድርበት ይሆን ብለን ላቀረብንለት ጥያቄ መስፍን ተከታዩን መልስ ሰጥቷል።

“ከሽንፈት ስትመጣና አሸንፈህ ስትመጣ አንድ አይደለም። በእርግጥ ግን እኛ አዕምሮአችን ላይ ትኩረት ያደረግነው በኢትዮጵያ ዋንጫ ላይ ነው። በሁለቱም ላይ ትኩረት እናደርጋለን ግን በይበልጥ ደግሞ በአቋራጭ ዋንጫ ልናነሳ የምንችለው በኢትዮጵያ ዋንጫ ስለሆነ ከመጀመሪያውም ትኩረት ያደረግነው እሱን ነው።”

ከፕሪሚየር ሊጉ በላይ ለኢትዮጵያ ዋንጫው ነበር በአመቱ መጀመሪያ ላይ ትኩረት ያደረጋቹት የሚለው ቀጣዩ ጥያቄያችን ነበር።

“መጀመሪያ የሊጉን ዋንጫ ማሳካት ነው። ግን ነገሮች አልፈቀዱልንም። እና በጎን ደግሞ የኢትዮጵያን ዋንጫ አቅደን ነው የመጣነው ይሄ(ፕሪሚየር ሊግ) ከሆነ ሆነ ካልሆነ የኢትዮጵያ ዋንጫ ብለን ነው የተነሳነው።”

መስፍን ታፈሰ ሲዳማ ቡናን ከመቀላቀሉ በፊት በኢትዮጵያ ቡና በነበረው ቆይታ በአምናው የፍፃሜ ጨዋታ ቡናማውን ማልያ ለብሶ ዋንጫውን አሸንፏል።

በቅፅል ስሙ ጩንኬ የሚል መጠሪያ ያለው መስፍን በአምናው የፍፃሜ ጨዋታ የገጠመውን ወላይታ ድቻን ከ336 ቀናት በኋላ በተመሳሳይ መድረክ ይገጥማል።

“የዋንጫ ጨዋታ ስጫወት ለሶስተኛ ጊዜ ነው። ሀዋሳም እያለሁ ከፋሲል ጋር ተጫውቻለሁ። አምናም በኢትዮጵያ ቡና እያለሁም ከወላይታ ድቻ ጋር ተጫውቼ ዋንጫ በልቻለሁ። አሁንም ከባድ ጨዋታ ነው። እኛም ደግሞ በዛ ልክ እየተዘጋጀን ነው ብዬ አስባለሁ።”

ሌሎችም ዋንጫ የማሸነፍ ታሪክ ያላቸው ተጫዋቾች በቡድኑ አሉ የሚለው መስፍን ልምዳቸውን ለሌሎች ተጫዋቾች እያካፈሉ ያላቸውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን እየተነጋገሩ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ጠቁሟል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን በርከት ያሉ በሊጉ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች አስፈርሞ ዓመቱን የጀመረው ሲዳማ ቡና በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር ላይ ለፍፃሜ ሲደርስ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በክለቡ ዙሪያ ይህንን ዋንጫ ለማሳካት ከፍተኛ ተነሳሽነት እና ጉጉት አለ ሲልም መስፍን ተናግሯል።

“ራሳችንም ትልቅ ታሪክ ሰርተን ማለፍ እንፈልጋለን። ለደጋፊዎችም ደግሞ ይህ ትልቅ ነገር ነው። ለኛም ታሪክ ነው ለነሱም ደግሞ እንደ ታሪክ የሚወራ ነገር ስለሆነ ከዚህ አኳያ በደንብ እየደገፉን ነው። እግዚአብሔር ብሎ ደግሞ ዋንጫውን ብናነሳ በጣም ደስተኛ ነኝ።”

ሁለቱ የፍፃሜ ተፋላሚዎች በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሊጉ ባደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ ሲዳማ ቡና ሲያሸንፍ በአንዱ ነጥብ ተጋርተዋል።

ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን ለማሸነፍ በምን ደረጃ እየተዘጋጀ ነው ለሚለው ጥያቄ የተለየ ዝግጅት አናደርግም የመስፍን መልስ ነው።

“እኛ እንደ ሌሎች ጨዋታዎች ነው የምንዘጋጀው ፤ የዋንጫ ጨዋታ ስለሆነ እዚህ ጋር አቻ መውጣት የለም። ማሸነፍ እና ማሸነፍ ነው። ያን ነገር ስለምናውቅ ትኩረታችን ሁሉ ዋንጫው ላይ ነው። በአጠቃላይ ለማሸነፍ በጥሩ እየተዘጋጀን ነው።”

በሁለቱ ክለቦች ያለፉት ዘጠኝ የሊጉ የእርስ በርስ ግንኙነትች ሲዳማ ቡና በወላይታ ድቻ አልተሸነፈም። ይህ ተከታታይ ውጤት ለሲዳማ ቡና ተጫዋቾች ተጨማሪ መነቃቃትን ፈጥሮ ይሆን ? መስፍን ተከታዩን ብሏል።

“ይሄ ጥሎ ማለፍ ነው። እንደዚል የሚባል ነገር የለውም። ነገሮችን ተመልሰን ማየት የለብንም። በጨዋታው ላይ ስራችንን ሰርተን ያን ነገር ማስቀጠል ነው ያለብን።”

የውድድር ዓመቱ እምብዛም በግሌ ጥሩ አልነበረም ያለው መስፍን ታፈሰ ነገሮች እንዳሰብኩት አይደለም ፤ የተወሰነ ጫናም ነበር ሲል ገልጿል።

መስፍን አክሎም እግዚአብሔር ብሎ ዋንጫውን ብናነሳ በህይወቴ በጣም ደስተኛ የምሆንበት ቀን ነው ሲል ተናግሯል።

ጨዋታውን ለመመልከት እና ቡድናቸውን ለማበረታት በርካታ ቁጥር ያላቸው ደጋፊዎች የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ስታድየም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መስፍን ታፈሰም ተከታዩን መልዕክት ለደጋፊዎች አስተላልፏል።

“ከኛ ጎን ይሁኑ ፣ እኛም አናሳፍራቸውም። በነርሱ ነው እዚህ የደረስነው። እነሱ አቅም ነው የሚሆኑን እና ተጨማሪ አቅምም ነው የሚጨምሩልን ደስተኛ ነኝ እነርሱ በመምጣታቸው እና በነርሱ ፊት በመጫወታችን።”

የውጤት ግምት መግለፁ ይቅርብኝ ያለው መስፍን በእርግጠኝነት እናሸንፋለን በሚል ደምድሟል።

በመጨረሻም መስፍን ታፈሰ ጨዋታው በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ለሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች እና በጨዋታው ተሳታፊ ለሆኑት መልዕክቱን አስተላልፏል።

“እግር ኳስ በርግጥ የፍቅር ነው። እየተዝናናህ የምታየው ነው። እንደዚህ አይነት ነገሮች ደስ አይሉም። እኛ ጋር ያለውንም ነገር እናስተካክላለን። ነገሮች ከኛም ከዳኛም ስለሚሄዱ መጠንቀቅ አለብን። ስፖርት ውስጥ ስሜታዊ ትሆናለህ። በእርግጥ ምንም ሊፈጠር ይችላል ግን መለስ ብለህ ስታይ ነው ሁሉም ነገር ታሪክ ሆኖ የሚያልፈው ከዚህ አኳያ በኛም በነሱም በኩል ሜዳ ላይ ጥሩ ነገር እናሳያለን ብዬ አስባለሁ።”

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ፍፁም ጥላሁን የሁለት ጨዋታ እገዳ ሲጣልበት አብርሃም ጌታቸው፣ ድልአዲስ ገብሬ፣ ፍፁም ፍትዓለው እና አሸናፊ ጥሩነህ እያንዳዳቸው የአንድ ጨዋታ እገዳ ተጥሎባቸዋል
Next Article “ወንድሞቻችን ሰርተው ያለፉትን ታሪክ እንደግመዋለን” “ፋሲል ከነማን ያሸነፍንበት ጨዋታ ትልቅ የሞራል ስንቅ ይሆነናል” “በደከምንም በበረታንም ሰዓት ከጎናችን ሆነው ይደግፉናል” “ለአንድ ሰዓት ያህል የከተማው መግቢያ ላይ ቆመን ስንጠብቅ ነበር” ቢንያም ገነቱ (ወላይታ ድቻ)

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችዕይታአዲሰ አበባ ስታዲየም

ታድሷል ተብሎ ያልታደሰ መሳዩ አንጋፋው ስታዲየም…!

ቴዎድሮስ ታከለ By ቴዎድሮስ ታከለ 4 months ago
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 4ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በቀጥታ ውጤት /LIVESCORE/ ይከታተሉ
የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ተጋጣሚውን አውቋል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ባካሄደው ውይይት ለረጅም ጊዜያት ተጓቶ የነበረውን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል
“ሁለተኛው አጋማሽ ላይ መረጋጋት ብቻ ነው ያደረግነው” “ቅዱስ ጊዮርጊስ በፕሪሚየር ሊጉ ጥሩ ተፎካካሪ ይሆናል ብዬ አስባለሁ” አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት – የመቻል ዋና አሰልጣኝ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?