የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. አብርሃም ጌታቸው (ቅዱስ ጊዮርጊስ) : ክለቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው የ33ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 83 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድርአመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ድልአዲስ ገብሬ (ድሬደዋ ከተማ) : ክለቡ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ33ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 66 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድርአመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. ፍፁም ፍትዓለው (ባህርዳር ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ባህርዳር ከተማ – ሲዳማ ቡና
- ስሁል ሽሬ – ባህርዳር ከተማ
- መቐለ 70 እንደርታ-ባህርዳር ከተማ
- ኢትዮጵያ ቡና – ባህርዳር ከተማ
- አዳማ ከተማ – ባህርዳር ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
- ማሰታውቂያ -

4. ፍፁም ጥላሁን (ቅዱስ ጊዮርጊስ) : ከታች በተጠቀሱት 9 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ቅዱስ ጊዮርጊስ-ፋሲል ከነማ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
- መቻል – ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ወላይታ ድቻ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ሀዲያ ሆሳዕና – ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ – አዳማ ከተማ
- ሃዋሳ ከተማ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ኢትዮጵያ መድን – ቅዱስ ጊዮርጊስ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2000 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
5. አሸናፊ ጥሩነህ (ኢትዮ ኤሌትሪክ ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ኢትዮ ኤሌትሪክ – ወላይታ ድቻ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ- አርባምንጭ ከተማ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ – ሐዋሳ ከተማ
- ወላይታ ድቻ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
6. አሰልጣኝ ካሊድ መሀመድ (ረዳት አሰልጣኝ) ሀዲያ ሆሳዕና / ክለቡ ከመቻልጋር በነበረው የ33ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በውድድር አመቱ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ቢጫ ካርድ ተመልክተዋል። ስለሆነም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 በተቁ 35 መሠረት አሰልጣኙ 1/አንድ ጨዋታ እንዲታገዱና ብር / 5000 /አምስት ሺህ / እንዲከፍሉ ወስኗል።


