የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. አስቻለው ታመነ (መቻል): ክለቡ ከሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ32ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 40 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋች አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ወንድሜነህ ደረጄ (ባህርዳር ከተማ) : ክለቡ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ባደረገው የ32ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 64 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. አለን ካይዋ (ኢትዮጵያ መድን ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ድሬደዋ ከተማ – ኢትዮጵያ መድን
- ኢትዮጵያ መድን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ ቡና – ኢትዮጵያ መድን
- ኢትዮጵያ መድን – ሲዳማ ቡና
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
- ማሰታውቂያ -
4. መስፍን ታፈሰ (ሲዳማ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ሲዳማ ቡና – ኢትዮጵያ መድን
- ሲዳማ ቡና – ኢትዮጵያ ቡና
- አርባምንጭ ከተማ – ሲዳማ ቡና
- ሲዳማ ቡና – ባህርዳር ከተማ
- ኢትዮጵያ መድን – ሲዳማ ቡና
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
5. ኬኔዲ ከበደ (ወላይታ ድቻ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ወላይታ ድቻ – ኢትዮጵያ ቡና
- ቅዱስ ጊዮርጊስ – ወላይታ ድቻ
- ሲዳማ ቡና – ወላይታ ድቻ
- ወላይታ ድቻ – መቻል
- ወላይታ ድቻ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
6. ሽመክት ጉግሳ (ኢትዮ ኤሌትሪክ ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ኢትዮ ኤሌትሪክ – ወላይታ ድቻ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ – ሀዲያ ሆሳዕና
- አርባምንጭ ከተማ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ-ሲዳማ ቡና
- ወላይታ ድቻ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
7. ራምኬል ጀምስ (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ኢትዮጵያ ቡና – ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ኢትዮጵያ ቡና
- መቻል – ኢትዮጵያ ቡና
- ኢትዮጵያ ቡና – ሲዳማ ቡና
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ – ኢትዮጵያ ቡና
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
8. ኪቲካ ጅማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ባህርዳር ከተማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- አርባምንጭ ከተማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ፋሲል ከነማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ድሬደዋ ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
9. አቤል አሰበ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ድሬደዋ ከተማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ድሬደዋ ከተማ – ኢትዮጵያ መድን
- ሀዲያ ሆሳዕና – ድሬደዋ ከተማ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ድሬደዋ ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
10. አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 10 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- አርባምንጭ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ – አዳማ ከተማ
- ሃዋሳ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ባህርዳር ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ – ፋሲል ከነማ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ – ድሬደዋ ከተማ
- አዳማ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
- ሀዲያ ሆሳዕና – ድሬደዋ ከተማ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ድሬደዋ ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ∶ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ
ቅጣት ብር 2000 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
11. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር በነበረው የ32ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንትን ፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበርን እና የኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝን በስም በመጥራት አፀያፊ ስድብ ስለመኣደባቸው ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም የከለቡ ደጋፊዎች ላጠፉት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 4(ሀ) ብር100 000 /አንድ መቶ ሺህ/እንዲከፍል የውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


