ሰባት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫዎች ባለቤቱ በይፋ ጫማውን ሰቀለ።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ለዋናው ቡድን በመጫወት ከክለቡ ጋር ስድስት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫዎችን አሳክቷል። ከልጅነት ክለቡ ፈረሰኛው ቤት ከ13 አመታት በኋላ በመለያየት በአዳማ (በሊጉ ባይጫወትም) ለመቻል ፣ እንዲሁም ላለፈው አንድ አመት ከግማሽ ወራቶች ያህል በኢትዮጵያ መድን አሳልፏል። በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከመድን ጋር ቻምፒዮን መሆን የቻለው ይህ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ እና የአማካይ ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ምንተስኖት አዳነ ከ17 አመታት በኋላ እግር ኳስን ማቆሙን አሳውቋል። 👇
“ላለፉት 17 ዓመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ መቆየቴ ይታወቃል በነበረኝ ቆይታ በጣም አመስጋኝ ነኝ ያለው ተጨዋቹ አሁን ጊዜው አዲስ የህይወት ምዕራፍ የምጀምርበት ነው በጣም ደስ የሚል እና ስኬታማ ጊዜ ነው የነበረኝ ለዚህም በተለያየ ጊዜ በክለብ እና በብሔራዊ ቡድን ” የሰራን አሰልጣኞች ተጨዋቾች ደጋፊዎች የህክምና ባለሙያዎች ኪት ማናጀሮች የቢሮ ሰራተኞች የፌዴሬሽን እና የክለብ የበላይ ሀላፊዎች ለነበረን መልካም ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ ብሏል።”
“ቤተሰቦቼ እናት አባቴ፣ ባለቤቴ ልጆቼ፣ እህት ወንድሞቼ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ላደረጋችሁልኝ ነገር ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ያለእናንተ ይሄ ሁሉ የማይታሰብ ነዉ። ለመላው የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች እና የክለቡ አመራሮች በነበረኝ 13 አመት ለሰጣችሁኝ አክብሮት ” ፍቅር እያመሰገንኩ እንደ አንድ በክለቡ እንዳደገ ልጅ አሁን ላይ ክለቡ ያለበት ሁኔታ ያሳስበኛል ብሏል። ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ ክለቡን የሚገልፅ እና በልኩ የተሰፋ አይደለም ለቅዱስ ጊዮርጊስ በልኩ የተሰፋዉ እና የሚያምርበት ውድድሮችን አሸንፎ ዋንጫ መቀበል ነዉ ከዚህ ውጪ ያሉት ነገሮች ክለቡን የሚመጥኑ አይደሉም ስለዚህ ልዩነታችሁን አጥብባችሁ ወደ አንድ ክለቡን ብቻ ወደሚጠቅም ሀሳብ እንድትመጡ እና ዳግም ክለቡን ወደ ነበረበት ክብር እንድትመልሱት ብዬ ማሳሰብ እፈልጋለሁ።


