መቻል ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተን የቀጠረው እና በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር በመግባት ያሬድ ካሳዬን የመጀመሪያ ፈራሚ ያደረገው መቻል ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን የግሉ አደረገ።
ሁለተኛው የክለቡ ፈራሚ ረመዳን የሱፍ ነው። የቀድሞው የምድረገነት ሽረ ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለገብ ተጫዋች ከኢትዮጵያ መድን ተከታታይ አመታት በኋላ ቀጣይ የእግር ኳስ ህይወቱ አራተኛው ክለብ መቻል ሆኗል።

ሌላኛው የክለቡ ሦስተኛ ፈራሚ የመሐል ተከላካዩ አማኑኤል ተርፉ ነው። የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኢራቁ አል ናፍጥር ክለብ ቆይታ የነበረው ይህ ተጫዋች ቀጣዩ መዳረሻው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ መቻል ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ