በዛሬው ዕለት ወደ ወሳኝ ዝውውር የገቡት መቻሎች የአራት ነባር ተጫዋቾችን ውል አደሱ።
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመሩት መቻል በዛሬው ዕለት በዝውውሩ የሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ቀደም ሲል የፈፀሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ውል ያጠናቀቁ አራት ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገልፀዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና በመቻል ያለፉትን ሁለት አመታት የቆየው የተከላካይ አማካዩ አማኑኤል ዮሐንስ ፣ የቀድሞው የአዳማ ከተማ እና ፋሲል ከነማ የመስመር አጥቂ በረከት ደስታ ፣ በኢትዮጵያ መድን ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና የተጫወተው አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ እና ከፋሲል ከነማ በኋላ በመቻል ላለፉት ሁለት አመታት ያሳለፈው የመስመር ተከላካዩ አለምብርሀን ይግዛው በክለቡ ለተጨማሪ ሁለት አመት ውላቸውን ያራዘሙ ነባር ተጫዋቾች ሆነዋል።
አስተያየት ይስጡ