መነሻ ገጽ መቻል መቻል ልምምድ የሚጀምርበት ቀን ታወቀ
መቻልዜናዎች

መቻል ልምምድ የሚጀምርበት ቀን ታወቀ

አጋራ
አጋራ

መቻል ነሐሴ 13 ልምምድ  ይጀምራሉ

አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ከሾሙ በኋላ ክለቡ ባለበት ክፍት ቦታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻለው መቻል የበረከት ደስታ ፣ ዳዊት ማሞ እና አማኑኤል ዮሐንስ ውል በማራዘም ጊኒያዊውን ግብ ጠባቂ መሐመድ ካማራ ፣ ላይቬሪያዊውን አማካይ ጄግባይ ሞሪስ ሱዳናዊውን ያህያ መሐመድ እና ሌላ ተጨማሪ የውጪ ዜጋን ጨምር ከሀገር ውጪ በረከት ካሌብ ፣ ያሬድ ካሳዬ ረመዳን የሱፍ ፣ አማኑኤል ተርፉ እና መክብብ ደገፉን ከሀገር ውስጥ እንዲሁም ሲሳይ ከበደን ረዳት አሰልጣኝ በማድረግ ቡድኑን ያጠናከረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ለዕረፍት ከሄዱበት አሜሪካ ወደ ሀገር ውስጥ የመጡት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጫዋቾቻቸው ጥሪ አድርገዋል። በዚህም መሠረት የፊታችን ማክሰኞ ነሐሴ 12/2018 ሁሉም የቡድኑ አባላት አዲስ አበባ ላይ ከተሰባሰቡ በኋላ በማግስቱ ዕሮብ ነሐሴ 13/2018 በቢሾፍቱ ከተማ ለ2019 የውድድር ዘመን የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ሀትሪክ ስፖርት ለማረጋገጥ ችላለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...