የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ በአሸናፊነታቸውን ቀጥለዋል

 

በአራተኛው ሳምንት የረፋድ መርሀ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስን ከ ሰበታ ከተማ ሲያገናኝ በፈረሰኞቹ የበላይነት ጨዋታው ሊጠናቀቅ ችሏል ።

የመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች ላይ ሁለቱም ቡድኖች ጠንካራ የመስመር ክፍላቸውን በመጠቀም የማጥቃት አማራጮችን ለመፍጠር ሲሞክሩ በሰበታ በኩል ኳስን መስረተው ለመጫወት ቢፈልጉም በተደጋጋሚ ከራሳቸው የጨዋታ ክፍል ውጪ ማለፍ ሳይችሉ ሲቆራረጥ ታይቷል ። ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያዎቹ አስራ አምስት ደቂቃዎች ላይ ከቀኝ የመስመር ክፍል ከሚነሱ ኳሶችን መከራዎችን ሲያደርጉ በዚህም አቤል ያለው ከ መስመር ያሻገረውን ኳስ አዲስ ግደይ ሞክሮ ፋሲል ያደነበት እንዲሁም ከ ማዕዘን ምት ያገኙትን ኳስ ፋሲል ገ/ሚካኤል አምልጦች ሮበርት ንግላንዴ መሬት ለ መሬት ሞክረውት የዳነባቸው ሙከራዎች ተጠቃሹ ነው ።

ፈረሰኞቹ ተደጋጋሚ የመስመር ሙከራቸው ፍሬ አፍርቶላቸው በዕለቱ ካለፉት ጊዜያት ወደ ፊት ተስቦ የማጥቃት እንቅስቃሴውን ሲያግዝ በነበረው ሄኖክ አዱኛ ያሻማትን ኳስ የሰበታው ሀይለ ሚካኤል አደፍርስ የፍፁም ሳጥን ውስጥ በእጁ ኳስ መንካቱን ተከትሎ የተገኘውን ኳስ ጌታነህ ከመረብ በማሳረፍ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ የፍፁም ቅጣት ምት ጎሉን በማስቆጠር ጊዮርጊስን መሪ ማድረግ ችሏል ።

ከግቡ መቆጠረ በኋላ እምብዛም ሙከራዎች ሳይደረጉበት ሲቀሩ ሰበታ ከተማዎች በተከላካያቸው አዲሱ ተስፋዬ ከሳጥን ወወጪ አክርሮ መቶ ፓትሪክ ማታሲ ካወጣበት ሙከራ ውጪ አስደንጋጭ ሙከራዎች ሳይደረጉበት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል ።

በሁለተኛው አጋማሽ በማጥቃቱ ረገድ ተሻሽለው ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ መቅረብ የቻሉት ሰበታ ከተማዎች ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርጉ አለማየሁ ሙለታ አሻግሮት እስራኤል እሸቱ ሞክሮት ወደ ውጪ የወጣበት የግብ እድል ተጠቃሹ ነው ። ከዚህ ሙከራ በኋላ ሰበታ ከተማዎች ተደጋጋሚ ታደለ መንገሻ አሾልኮ ያቀበለውን ኳስ እስራኤል እሸቱ ሰበታን አቻ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፏል ።

በተደጋጋሚ ከግቡ መቆጠር በኋላ ወደ ግብ መሄድ የቻሉት ሰበታ ከተማዎች ቡልቻ ሹራ ከመስመር አሻግሮለት ጥሩ ሲነቀሳቀስ የነበረው እስራኤል ሳይጠቀምበት የቀረው የግብ ዕድል የምታስቆጭ ለግብ የቀረበች አጋጣሚ ነበረች ። ወደ ጨዋታ እንቅስቃሴ ዘግየት ብለው በሁለተኛው አጋማሽ የገቡት ፈረሰኞች አከታትለው ሁለት ግቦችን በደቂቃ ልዩነት ማስቆጠር ችለዋል ።

የሰበታ የተከላካይ ክፍል አዲሱ ተስፋዬ የሰራውን ስህተት ከሳጥን ውጪ ያገኘው አቤል ያለው አክርሮ ከሳጥን ውጪ በመምታት ጊዮርጊስን መሪ ሲያደርግ ከደቂቃዎች ልዩነት በኋላ አቤል ያለው ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አዲስ ግደይን ቀይሮ መግባት የቻለው ጋዲሳ መብራቴ በግሩም ሁኔታ ከመረብ በማሳረፍ መሪነታቸውን ወደ ሶስት ከፍ ማድረግ ችለዋል ።

 

ከግቡ መቆጠር በኋላ ሁለቱም ቡድኖች ተቀዛቅዘው ቢቆዩም ጌታነህ ከበደ የግል አቅሙን በመጠቀም የሰበታ የተከላካይ ክፍል ላይ በፍፁም ሳጥን ውስጥ ጫና በመፍጠር የውድድር ዓመቱን በግሉ አራተኛ ግብ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል ።

ከሶስተኛ ግብ መቆጠር በኋላ የተዳከሙት ሰበታዎች የማጥቃት አማራጫቸውን በማስፋት ፍፁም ገ/ማርያም እና ቃልኪዳን ዘላለምን ቀይረው ማስገባት ችለዋል ።አብዛኛውን የማጥቃት አማራጫቸውን ከግራ መስመር ቡልቻ ሹራ ከሚነሱ ኳሶች አመዝነው ሙከራዎችን ሲያደርጉ ቡልቻ አሻግሮለት ቃልኪዳን ዘላለም በሁለት አጋጣሚዎች ሳይጠቀምበት የቀሩባቸው አጋጣሚዎች በሰበታ በኩል የሚጠቀሱ ሙከራዎች ነበሩ ።

አልፎ አልፎ ወደ ግብ ክልል ይደርሱ የነበሩት ሰበታ ከተማዎች ተቀይሮ የገባው ፍፁም ገ/ማርያም የግል ብቃቱን እና ልምዱን ተጠቅሞ በፍፁም ሳጥን ውስጥ በፍሪምፖንግ የተሰራበትን ጥፋት ወደ ግብ በመቀየር ከሽንፈት ያልታደገቻቸውን ግብ ከመረብ ለማሳረፍ ችሏል።

 

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን መምራት ሲችሉ ሰበታ ከተማዎች በሰባተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor