የጨዋታ ዘገባ | ሰበታ ከተማዎች ወደ ድል የተመለሱበትን ሀዋሳ ላይ አስመዝግበዋል

 

በሁለተኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ሰበታ ከተማን እና ሀዋሳ ከተማን አገናኝቶ በሰበታ ከተማ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በተሻለ መልኩ የሰበታ ከተማ ብልጫ የታየበት የመጀመሪያ ግማሽ የኳስ ቅብብሎች የበዙበት ነበር። ላውረንስ ለሜንሳህ በጭንቅላቱ ገጭቶ በአግባቡ ባለማቀበሉ ፉአድ አገባው ሲባል ሜንሳ ያደናበት አስቆጪ አጋጣሚ ነበረች።

መጠነኛ ብልጫቸውን የተጠቀሙት ሰበታዎች ቡልቻ ሹራ ላይ በተሰራው ጥፋት የተገኘችውን የቅጣት ምት ፉአድ ፈረጃ አሻምቶ ቋሚው ለትማ ስትመለስ ያገኛት አለማየሁ ሙለታ በሚገባ ተጠቅሞ ባስቆጠራት ግብ መሪ ሆነዋል።

ከኳስ ቅብብሎች በዘለለ ተጨማሪ ግቦች ሳይቆጠሩ የመጀመሪያው አጋማሽ በሰበታ ከተማ 1-0 መሪነት ለእረፍት ወጥተዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ አቻ ለመሆን የጣሩት ሀዋሳ ከነማዎች ሲያገኟቸው ከነበሩት የማእዘን ምት በመጠቀም። ከማእዘን የተሻማውን ኳስ መስፍን ታፈሰ በግንባሩ ገጭቶ ባስቆጠራት ግብ አቻ ለመሆን ችለዋል።

ያልተቀናጀው የሀይቆች የተከላካይ ስፍራ ዋጋ ከማስከፈል አላዳናቸውም አስራ ስድስት ከሀምሳ ቡልቻ ሹራ ላይ በተሰራው ጥፋት የተገኘችውን የፍፁም ቅጣት ምት በሚገባ በመጠቀም ዳዊት እስጢፋኖስ በድጋሚ ሰበታን መሪ አድርጓል።

ከመሀል ሜዳ መሬት ለመሬት የተላከችውን ኳስ የሰበታ ተጫዋቾች ሳይደርሱባት ቀድሞ ለማስጣል ሰሆህ ሜንሳህ ከግብ ክልሉ ወጥቶ ሸርተቴ በመውረድ ኳሷን ለማራቅ ሲሞክር በቅርብ ርቀት የነበረው ፉአድ ፈረጃ አግንቶ በረጅሙ ለግቶ ግቧን በማስቆጠር ልዩነቱን ከፍ አድርጓል።

 

ጨዋታው በሰበታ ከተማ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ በአንደኛው ሳምንት ነጥብ ከጣሉ በኋላ ወደ አሸናፊነት ሲመለሱ ሀይቆች አመቱን በሽንፈት ጀምረዋል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team