መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | ድሬዳዋ ከተማ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | ድሬዳዋ ከተማ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ

አጋራ
አጋራ

 

ወላይታ ድቻን እና ድሬድዋ ከተማንያገናኘው የአምሰተኛ ሳምንት መርሀ ግብር በድሬዳዋ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ኳስን ተቆጣጥረው በመጫወት ወደ ግብ ለመድረስ ሚዛን የያዙት ሁለቱም ቡድኖች። በአብዛኛው ኳስን ተቆጣጥረው በሚጫወቱበት ስአት ከብዙ ቅብብል ውጭ ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ሰብረው ለመግባት ያስቻላቸው አልነበረም።
ስንታየሁ መንግስቱን ተጠቅመው ወላይታ ድቻ የመጀመሪያውን ጥቃት ሰንዝረዋል። በዚህ አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች በኩል በበጎ ጎኑ ሊነሳ የሚችለው የተገኙ የቅጣት ምቶች ወደ ግብነት ለመቀየር የተደረጉ ጥረቶች ናቸው። ለምሳሌነትም ሙህዲን ሙሳ ላይ በተሰራችው ጥፋት የተገኘችውን ቅጣት ምት ኤልያስ ማሞ መትቶ ኳሷ ቋሚዊውን ለትማ የተመለሰችበት እና 13ኛው ደቂቃ ላይ በረከት ሳሙኤል ከቅጣት ምት መሬት ለመሬት መትቶ በድቻ ተከላካዮች የተጨረፈችውን ኳስ ያገኘው አስቻለው ግርማ ግብ አድርጎ ቡርትካናማዎችን ቀዳሚ ያደረገበት ተጠቃሾች ናቸው።

 

ሌላኛው በጦና ንቦች በኩል የምትጠቀሰው ስኬታማ የቅጣት ምት አማኑኤል ተሾመ በቀጥታ ወደ ግቡ ያሻማውን ኳስ ተጠቅሞ ቸርነት ጉግሳ በግንባሩ ገጭቶ ግብ ጠባቂው ፍሬው ጌታሁን ለጥቂት ባያወጣት አቻ ልታደርጋቸው የምትችል አጋጣሚ እንደነበረች መጥቀስ ይቻላል።

በጨዋታ ሂደት ወላይታ ድቻዎች አቻ መሆን የቻሉበትን ግብ አግኝተዋል ስንታየሁ መንግስቱ ያቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ ፀጋዬ ብርሀኑ ማስቆጠር ችሏል።


እዮብ በቃታ በአግባቡ ሳይቆጣጠራት የቀረውን ኳስ ያገኘው ኤልያስ ማሞ ተቆጣጥሮ ለሙህዲን ሙሳ አቀብሎት በአግባቡ በመጠቀም ሙህዲን በድጋሚ ድሬድዋን መሪ አድርጎ በድሬዳዋ 2-1 መሪነት ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።


በሁለተኛው አጋማሽ ኳስን የመቆጣጠር ፍላጎት በሁለቱም ቡድኖች በኩል ቢኖርም ረብ የለሽ ሲሆን ተስተውሎ ቀዝቀዝ ያሉ እንቅስቃሴዎችን የተመለከትንበት ቢሆንም አልፎ አልፎም ቢሆን ሁለቱም ቡድኖች ሙከራዎችን ከማደርግ አልተቆጠቡም።

እንደመጀመሪየው ግማሽ ሁሉ የቅጣት ምቶች ወደ ግብ የመቀየር ፍላጎት በሁለተኛው ግማሽም ሲተገበር ተስተውሏል። በጦና ንቦች በኩል እዮብ በቃታ ከቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ ቢመታውም ፍሬው ጌታሁን በግሉ ብቃት ለጥቂት ሲያወጣበት።

በድሬዳዋ በኩል ደግሞ ደንኤል ደምሴ ከግራ ሳጥኑ ያሻማለትን እዮብ አለማየሁ አግብቸዋለሁ ብሎ በልበ ሙሉነት በግንባሩ የገጫት ኳስ ለጥቂት በአግዳሚው የወጣቺው ኳስ በዲቻ በኩል እጅግ በጣም አስቆጪ ነበረች። ከዚህ ውጭ ይህ ነው ሊባሉ የማይችሉ ሙከራዎችም ይሁን ለግብነት የተቃረቡ እድሎች አልተፈጠሩም። በድሬድዋ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ጨዋታው መቋጫውን አግኝቶ ቡርትካናማዎቹ ተከታታይ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...