የጨዋታ ዘገባ | ኢትዮጵያ ቡና በአቡበከር ናስር ሀትሪክ ሸገር ደርቢን በድል ተወጥቷል

 

የ6ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማሮ የሆነው ሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቡና 3-2 በሆነ ውጤት ተረትቷል።

በመጀመሪያዎቹ አጋማሽ የተረጋጋ የኳስ ቁጥጥር በኢትዮጵያ ቡና በኩል ሲደረግ ቅዱስ ጊዮርጊሶችም ኳስን መሰረት አድርገው በመጫወት አልፎ አልፎም ቢሆን ረጃጅም ኳሶች ወደ ተቃራኒ ቡድን ለመድረስ ጥረዋል። ፓትሪክ ማታሲ ጀምሩ አስራ ስድስት ከሀምሳ ውስጥ አቡበክር ናስር ላይ በሰራው ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ሲወገድ ፈረሰኞቹ ከጀምሩ በጎደሎ ለመጫወት ተገደዋል።

ሮቢን ንጋላንዴ በማስወጣት በፓትሪክ ማታሲ ምትክ ለአለም ብርሀኑን በግብጠባቂነት አስገብተዋል። የተገኘችውን የፍፁም ቅጣት ምት እራሱ አቡበከር ናስር አስቆጥሮ ቡናን መሪ አድርጓል።


ከግብ ጠባቂ ጀምሮ ኳስን መስሻንቆ ሲጫወቱ የነበሩት ቡናማዎቹ ስህተት ከመስራት አላደናቸውም ሬድዋን ናስር ለግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ አቀብላለው ብሎ በራሱ ላይ አስቆጥሮ ፈረሰኞቹ አቻ መሆን ችለዋል።

በአፋጣኝ አፀፋዊ ምላሽ የሰጡት ኢትዮጵያ ቡናዎች በድጋሚ መሪ ሆነዋል። አቤል ከበደ ሳጥን ውስጥ ያቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ አቡበክር ናስር ለራሱ ለበድኑም ሁለተኛዋን ግብ አስቆጥሯል።

ጨዋታው አስፈሪ ባይሆንም ተከታታይ ግቦች ከማስተናገድ ግን አልተቆጠበም። አቤል ያለው በግል ብቃቱ ኳስ እየገፋ ሄዶ ሳጥን ውስጥ ለነበረው ጋዲሳ መብራቴ አቀብሎት ኳስ እና መረብን በማገናኘት በድጋሚ ቅዱስ ጊዮርጊሶችን አቻ አድርጓል። ሁለቱም ቡድኖች ተጨማሪ ግቦችን ለማስቆጠር ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቶ የመጀመሪያው አጋማሽ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

 

በሁለተኛው አጋማሽ ቶሎ ቶሎ በመድረስ የተሻሉ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች 48ኛው ደቂቃ አስቻለው ታመነ እራሱ አቡበከር ናስር ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘው የፍፁም ቅጣት ጥን ሳይጠቀምባት ቀርቶ ሀትሪክ የሚሰራበት እድልም አምክኗል። ከዛ በተጨማሪም ከታፈሰ ሰለሞን መሬት ለመሬት ሳጥን ውስጥ የተላከችለት ኳስ አስቆጠረው ሲባል ሄኖክ አዱኛ ለጥቂት አውጥቶበት በድጋሚ ሀትሪክ የመሰራት እድሉ ህልም አድርጎበታል።

 

በሌላ በኩል በጎደሎ እንደመጫወታቸው መጠን ፈረሰኞቹ ያላቸውን ነጥብ ለማስጠበቅ ወደ ኋላ አፈግፍገው ተጫውተዋል። መጠነኛ ፍጥነት ያለው ኳስን መቆጣጠር አድርጎ በመጫወት ቶሎ ቶሎ ወደ ተጋጣሚ ቡድን በመድረስ የማሸነፊያ ግብ ተጫዋች የነበሩት ቡናማዎች በአቡበክር ናስር የማሸነፊያ ግብ አስቆጥረዋል። ለግብ በኋላ አቡበክር ናስር ከሙጂብ ቃሲም ቀጥሎ ሀትሪክ የሰራ ሁለተኛ ተጫዋች ሆኗል። በዚህኛው አጋማሽ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችና ግብ መሆን የሚችል ኳስ በተቃራኒ ቡድን ላይ ሳይሰነዝሩ ወጥተዋል። ጨዋታውም በኢትዮጵያ ቡና 3-2 አሸናፊነት መጠናቀቅ ችሏል።

 

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor