By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የጨዋታ ዘገባ | ጅማ አባጅፋር ከተከታታይ አራት ጨዋታዎች ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል
Share
Notification Show More
Latest News
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችጅማ አባጅፋርየጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

የጨዋታ ዘገባ | ጅማ አባጅፋር ከተከታታይ አራት ጨዋታዎች ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 4 years ago
Share
SHARE

በ13ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ በቅድሚያ የተደረገው የወላይታ ድቻ እና ጅማ አባ ጅፋር ጨዋታ እዮብ አለማየሁ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ ጅማ አባጅፋሮች አሸንፈዋል ።

ወላይታ ድቻ በ13ኛው ሳምንት መከላከያ በረቱበት ጨዋታ ከተጠቀሙት አሰላለፍ አንድ ለውጥ ብቻ አድርገው የገቡ ሲሆን በያሬድ ዳዊት ምትክ ምንይሉ ወንድሙ የመሰለፍ ዕድልን ያገኘ ሲሆን በጅማ አባጅፋር በኩል ደግሞ በሳምንቱ በሲዳማ ቡና በተሸነፉበት ጨዋታ ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ ሶሰት ቅያሪዎቸን በማድረግ አላዛር ማርቆስ ፣ አዛህሪ አልመሀዲን እና ዳዊት ፍቃዱን በማሰለፍ ዮሀንስ በዛብህ ፣ በላይ አባይነህ እና ዱላ ሙላቱ በተቀያሪ ወንበር አስቀምጠው ጨዋታውን ጀምረዋል ።

- ማሰታውቂያ -

በሁለቱም በኩል በሚደረግ ጥሩ የማጥቃት እንቅስቃሴ የጀመረው ጨዋታ ኳሶች ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ክልል የሚደርሱበት ነበር ። ጅማ አባጅፋሮች ኳሱን ይዘው በመጫወት ወደ ግብ ለመቅረብ ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን በወላይታ ድቻ በኩል ደግሞ በረጃጅም እና ፈጣን ኳሶች የጅማ አባጅፋርን የተከላካይ ክፍል ለመፈተን ችለዋል ።

ጠንካራ የግብ ሙከራዎችን ለማስመልከት ደቃቃዎችን ያስጠበቀው ይህ ጨዋታ 16ኛው ደቂቃ ላይ በወላይታ ድቻ በኩል ጥሩ የግብ ዕድል አሰመልክቶናል ። ከወላይታ ድቻ የሜዳ ክፍል በረጅም የተላከውን ኳስ በስንታየሁ መንግስቱ ተገጭቶ የደረሰው ቃልኪዳን ዘላለም በሳጥን ውስጥ ሆኖ ወደ ግብ የሞከረው ኳስ በግብ ጠባቂው አላዛር ሽመልስ ተመልሷል ። ከሶሰት ደቂቃዎች በኋላ ከምንይሉ የደረሰውን ኳስ ለግቡ ትይዩ የነበረው ስንታየሁ መንግስቱ አክርሮ ቢመታውም በድጋሚ በአላዛር ተመልሷል ። በተከታታይ ደቂቃዎች ጠንካራ የግብ ሙከራዎችን ያመከነው የጅማ አባጅፋሩ ግብ ጠባቂ አላዛር ሽመልስ በ22ኛው ደቂቃ ላይም በቃልኪዳን ዘላለም የተሞከረበትን ኳስ በማምከን ቡድኑን ታድጓል ።

በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ኳሱን ተቆጣጥረው ወደ ፊት ለማለፍ ሲታትሩ የነበሩት ጅማ አባጅፋሮች ቀስ በቀስ በጦና ንቦቹ በተፈጠረባቸው ጫና ወደ ኋላ ለመመለስ የተገደዱ ሲሆን በ34ኛው ደቂቃ ላይ ግን የነጠቁትን ኳስ በመልሶ ማጥቃት ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በመውሰድ ኳስ እና መረብን አገናኝተዋል ። በፈጣን የመጣለትን ኳስ በግራ መስመር የነበረው መሀመድኑር ናስር በጥሩ ሁኔታ ለእዮብ አለማየሁ አቀብሎት እዮብ ማስቆጠር ችሏል ። የመጀመሪያው አጋማሽም በጅማ አባጅፋር መሪነት ተጠናቋል ።

ጅማ አባጅፋሮች የሁለተኛውን አጋማሽ በጥሩ መልኩ መጀመር አልቻሉም ነበር ። ለግቡ መቆጠር አስተዋፅኦ ያበረከተውን የአጥቂ መስመር ተጫዋቻቸውን መሀመድኑር ናስርን በጉዳት ምክንያት ጨዋታውን መቀጠል ያልቻለ ሲሆን ምስጋናው መላኩ ተክቶት ገብቷል ። በአጋማሹ በመመራት ላይ የነበሩት ወላይታ ድቻዎች ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ደርሰው የአቻነቱን ግብ ለማግኘት ጥረቶችን ያደረጉበት ቢሆንም ወደ ጅማ አባጅፋር የግብ ክልል የሚደርሱ ኳሶች በቀላሉ በተከላካዮች ይመለሱ ነበር ። በጅማ አባጅፋር በኩልም በተወሰኑ አጋጣሚዎች ወደ ወላይታ ድቻ የሜዳ ክፍል ከመድረሳቸው ውጫ አብዛኛውን ጊዜ በመከላከሉ ላይ አተኩረው ተጫውተዋል ።

ምነም እንኳን የጦና ንቦቹ ወደ ጅማ አባጅፋር የግብ ክልል ከመስመር በሚነሱ እና በረጅም ወደ ሳጥን በሚላኩ ኳሶች ወደ ግብ ለማግኘት ጥረቶችን ያደረጉ ቢሆንም አንድም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ሳያደርጉ ነበር ሁለተኛውን አጋማሽ ያጠናቀቁት ። በጅማ አባጅፋር በኩል በ90+2 ላይ በእዮብ አለማየሁ አማካኝነት ሁለተኛ ግብ ለማስቆጠር ተቃርበው የነበረ ቢሆንም እዮብ በግብ ጠባቂው አናት ላይ አሳልፎ የነበረውን ኳስ በረከት ወልደዮሀንስ ደርሶ አውጥቶታል ። በመጨረሻም ጅማ አባጅፋሮች በ1 ለ 0 ውጤት አሸንፈው ጨዋታው ተጠናቋል ።

ውጤቱን ተከትሎ ጅማ አባጅፋር ነጥቡን 10 በማድረስ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት የሚያደርገውን ጉዞ የቀጠለ ሲሆን ወላይታ ድቻ በበኩሉ በ22 ነጥብ ባለበት 4ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።

በ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ ሀድያ ሆሳዕናን ጅማ አባጅፋር ደግሞ ወልቂጤ ከተማን የሚገጥሙ ይሆናል ።

You Might Also Like

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የጨዋታ ዘገባ | ጦሩ ድል ቀንቶታል
Next Article ፋሲል ከነማ ሙጂብ ቃሲምን አስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ አስፈርሟል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የአፍሪካ ዋንጫዋልያዎቹየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንዜናዎችአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ሽመልስ በቀለ ቅድመ ጨዋታ መግለጫ ሰጥተዋል

hatricksport team By hatricksport team 3 years ago
የ8ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
​ዘወትር ማክሰኞ በገበያ ላይ በመዋል ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ባለቀለሟ ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟም 
“የአዘጋጅ ከተማ ክለቦች በሜዳቸው ነጥብ የሚጥሉበትን ልማድ እኛ እንቀርፋለን ብዬ አስባለሁ” አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ
የሲቲ ካፑ የመዝጊያ ፕሮግራም በማርዮት ሆቴል ሊካሄድ ነው
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?