ፋሲል ከነማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት በቻለበት የ2013 የዉድድር አመት ቁልፍ የነበረዉ እና ከዉድድር አመቱ መገባደድ በኋላ የፕሮፌሽናልነት ዕድል አጊኝቶ በክረምቱ የተጫዋች የዝዉዉር መስኮት ወደ አልጄሪያዉ ጄኤስ ካቢሌ አምርቶ የነበረዉ አጥቂዉ ሙጅብ ቃሲም በአልጄሪያዉ ክለብ ከነበረዉ የ4 ወራት ቆይታ በኋላ በስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይቶ በዛሬዉ ዕለት ለቀድሞ ክለቡ ፋሲል ከነማ በድጋሚ መፈረሙ ተረጋግጧል።
ሁለገቡ አጥቂ ሙጂብ ቃሲም ከዚህ ቀደም ሶስት ዓመታትን ባሳለፈበት ፋሲል ከነማ ቤት ቀጣዮቹን ስድስት ወራት ማለትም እስከ ሰኔ 30 ድረስ ለመቆየት ፊርማዉን እንዳኖረም ለማወቅ ተችሏል።