መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ የሊጉ መሪ መሆን የቻለበትን ጣፋጭ ድል አስመዝግበዋል
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ የሊጉ መሪ መሆን የቻለበትን ጣፋጭ ድል አስመዝግበዋል

አጋራ
አጋራ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከተማን በአቤል ያለው እና በእስማኤል ኦሮ ኦጎሮ ሁለት ሁለት ግቦች 4 ለ 0 በሆነ ውጤት ሰፊ ውጤት አሸንፏል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በዘጠነኛው ሳምንት ጨዋታ ጅማ ጅፋርን ባሸነፉበት ጨዋታ የተጠቀሙትን ቋሚ አሰላለፍ ምንም ሳይቀይሩ የገቡ ሲሆን ፋሲል ከተማ ደግሞ መከላከያን ባሸነፉበት ጨዋታ ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ በከድር ኩሊባሉ እና በናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ቦታ አስቻለው ታመነን እና ሱራፌል ዳኛቸውን ወደ ቋሚ 11 መልሰው ጨዋታውን ጀምረዋል ።

በብዙ የተጠበቀው ጨዋታ በሜዳ ላይም ጥሩ እንቅስቃሴ በማሳየት ነበር ጅማሮውን ያደረገው ። ፋሲል ከተማዎች ኳሱን በመያዝ ከኋላ በመጀመር በተለየም በቀኝ መስመር በኩል ለማጥቃት ጥረቶችን ቢያደርጉም የቅዱስ ጊዮርጊስ የተደራጀ መከላከል ለፋሲል ከተማዎች ከባድ ነበር ።

ቅዱስ ጊዮርጊሶች በተለይም የሚነጠቁ ኳሶችን በፈጣን ሽግግር ወደ ፋሲል ከተማ ሜዳ በመውሰድ እና የፋሲል ከተማ የተከላካይ መስመር መልሶ ቅርፁን ሳይዝ በማጥቃት የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ችለው ነበር ። በጨዋታው የመጀመሪያው ሙከራ በእስማኤል ኦሮ ኦጎሮ አማካኝነት የተደረገ ነበር ። ቻርለስ ሉክዋጎ በረጅም የመታውን ኳስ ኦሮ ኦጎሮ በጥሩ ሁኔታ ተቆጣጥሮ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ በግብ ጠባቂው ሳማኪ ሚካኤል ተመልሷል ።

በ10ኛው ደቂቃ ላይ ፋሲል ከተማዎች ያገኙትን የማዕዘን ምት በመመለስ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ይዘው የገቡት ፈረሰኞቸለ በአማኑኤል ገብረሚካኤል አቀባይነት እና በአቤል ያለው ጨራሽነት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጠሩ ። በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ሲያሳዩ የነበረው የተደራጀ ማጥቃት እና መከላከል አስበው የገቡትን አጨዋወት በትክክል እየተገበሩ እንደነበር ዋና ማሳያ ነበር ።

የፈረሰኞቹን የተከላካይ ክፍል ሰብረው ለመግባት በዕጅጉ የተቸገሩት አፄዎቹ 20ኛ ደቂቃ ላይ በሱራፌል ዳኛቸው አማካኝነት ከቅጣት ምት ጥሩ ሊባል የሚችል ሙከራ አድርገው ነበር ። በተመሳሳይ እንቅስቃሴ የቀጠለው ጨዋታ 39ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ግብ ተቆጥሮበታል ። አቤል ያለው የነጠቀውን ኳስ ለኦሮ አጎሮ አቀብሎ በፍጥነት ሮጦ በድጋሚ የተቀበለውን ኳስ በግሩም አጨራረስ ግብ በማድረግ ለራሱም ሆነ ለክለቡ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል ።

ፋሲል ከተማዎች በቀኝ መስመር በኩል አድልተው በመንቀሳቀስ አልፈው ለመግባት እና ወደ ግብ መስመር ኳሶችን በማሻገር የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ያደረጓቸው ጥረቶች በፈረሰኞቹ ተከላካዮች በተደጋጋሚ ተመልሶባቸዋል ። የመጀመሪያው አጋማሽም በቅዱስ ጊዮርጊስ የ2 ለ 0 መሪነት ተጠናቀቀ ።

በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በመጀመሪያው አጋማሽ የነበራቸውን እንቅስቃሴ በጥሩ መልኩ በማስቀጠል መጫወት የቻሉበት ሲሆን ፋሲል ከተማዎች ደግሞ በተለይም በአጋማሹ የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ ወደ ፈረሰኞቹ የግብ ክልል መቅረብ የቻሉባቸውን አጋጣሚዎች ቢፈጥሩም የግብ ሙከራዎችን ለማድረግ ተቸግረው ነበር ።
52ኛ ደቂቃ ላይ ኦኪኪ አፎላቢ ሳጥኑ ጫፍ ላይ ወደ ግብ የሞከረው ሙከራ በቀላሉ በቻርለስ ሉክዋጎ በቀላሉ ተመልሷል ።

57ኛ ደቂቃ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ጥሩ የግብ ዕድል መፍጠር ችለው ነበር ። የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሱሌማን ሀሚድ በረጅም የመታውን ኳስ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከተከላካዮች ጀርባ አምልጦ በመግባት ካገኘው በኋላ ግብ ጠባቂው መውጣቱን ተከትሎ ለእስማኤል ኦሮ ኦጎር ቢያቀብለውም አጥቂው ኳሱ ላይ መድረስ ሳይችል ቀርቷል ። በዚህ አጋጣሚ ከግብ ጠባቂው ሳማኪ ሚካኤል ጋር የተጋጨው አማኑኤል ገብረሚካኤል ተጎድቶ ከሜዳ ወቷል ።

በ63ኛ ደቂቃ ላይ በአማኑኤል ገብረሚካኤል ተቀይሮ የገባው ቸርነት ጉግሳ ከሱሌማን ሀሚድ የደረሰውን ረጅም ኳስ ይዞ በመግባት ወደ ግብ ያደረገው ሙከራ የግቡን ቋሚ ሲመልስበት በቅርብ የነበረው ኦሮ ኦጎሮ አስቆጥሮ የቅዱስ ጊዮርጊስን መሪነት ወደ 3 ለ 0 ከፍ አደረገ ።

የአምና ሻምፕዮኖቹ ፋሲል ከተማዎቸ በፈጣን መልሶ ማጥቃት እና በረጃጅም ኳሶች የሚደረጉትን የቅዱስ ጊዮርጊስ የማጥቃት እንቅስቃሴ ለመገደብ በእጀጉ ተቸግረው ነበር ። በጨዋታ እንቅስቃሴ ላይ ከኋላ መስመር ላይ የተፈጠሩት ክፍተቶች ይህን በግልጽ ያመላከቱ ነበሩ ። በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ ሱራፌል ዳኛቸው ከሳጥን ውጪ ወደ ግብ ሞክሮ በግብ ጠባቂው እና በግቡ አግዳሚ የተመለሰበት ኳሶች በአፄዎቹ በኩል የታዩ የግብ ዕድሎች ነበሩ ።

መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ አራተኛው ዳኛ ተጨማሪ አራት ደቂቃዎች ካሳዩ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ሌላ ግብ ማግኘት ችለዋል ። ከፈረሰኞቹ የሜዳ ክፍል በረጅም የተመታውን ኳስ አምበሉ ያሬዴ ባየህ በጭንቅላት ገጭቶ ለአስቻለው ታመነ ቢያቀብለውም የቀድሞው የፈረሰኞቹ ተጫዋች ለግብ ጠባቂው ሳማኪ ሚካኤል ለማቀበል ሲሞክር እስማኤል ኦሮ ኦጎሮ አግኝቶ ለራሱ ሁለተኛ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ አራተኛውን ግብ አስቆጠረ ። ይህን ተከትሎም ኦሮ ኦጎሮ በሊጉ ያስቅጠራቸውን ግቦች 7 ማድረስ ችሏል ።

ጨዋታውም በቅዱስ ጊዮርጊስ የ4 ለ ዐ አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን አፄዎቹ በውድድር አመቱ በዘጠኝ ጨዋታ ያስተናገዱትን ያህል ግብ በአንድ ጨዋታ የተቆጠረባቸው ሲሆኖ ወደ ሊጉ ከመጡ በኋላም በአራት ግብ ልዩነት ሲሸነፉ የመጀመሪያቸው ሆኖ ተመዝግቧል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 20 በማድረስ የሊጉ አናት ላይ ሲቀመጥ ከጨዋታው በፊት የሊጉ አናት ላይ የነበረው ፋሲል ከተማ ባለበት 18 ነጥብ ወደ 2ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...