የጨዋታ ዘገባ | ሲዳማ ቡና የ3 ለ 0 ድል ተጎናፅፏል

በጨዋታው በሁለቱም በኩል ተመጣጣኝ የሚባል የሜዳ ላይ ፉክክር የነበረ ሲሆን ወደ ግብ በመድረስ ግን ሲዳማ ቡናዎች የተሻሉ ነበሩ ። ለዚህም ፍሬው ሰለሞን በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ ሁለት ጊዜ በግቡ ቋሚ የተመለሱበት ሙከራዎቹ ተጠቃሽ ናቸው ።

በድሬዳዋ ከተማ በኩል ኳሱን ከኋላ መስርተው ለመውጣት ቢሞክሩም ለአጥቂዎቻቸው ትክክለኛ ኳሶችን በማድረስ በኩል ደከም ብለው ታይተዋል ። በጨዋታው 33ኛ ደቂቃ ላይ የሲዳማ ቡናው አጥቂ ይገዙ ቦጋለ ከግራ መስመር ተከላካዩ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ከመረብ በማሳረፍ ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ቻለ ።

ከግቧ መቆጠር በኋላ ድሬዳዋ ከተማዎች በተደጋጋሚ ወደ ሲዳማ የግብ ክልል መድረስ ቢችሉም ይህ ነው የሚባለሰ የግብ ሙከራ ሳያደርጉ ነበር የመጀመሪያው አጋማሽ የተጠናቀቀው ።

በሁለተኛው ኢጋማሽ የጨዋታው መሪዎች ጫና ፈጥረው መጫወት የቻሉ ሲሆን በተለያየ አጋጣሚም የተጋጣሚያቸውን የግብ ክልል በመድረስ ሁለተኛ ግብ ለማከል ጥረዋል ።

በድሬዳዋ ከተማ በኩል በተፈጠረባቸው ጫና ወደኋላ ተጠግተው ቢጫወቱም አልፎ አልፎ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ዕድሎችን ለመፍጠር ሞክረው ነበር ። በጨዋታው 79ኛ ደቂቃ ላይ ሲዳማ ቡና መሪነቱን ወደ 2 ለ 0 ማሳደግ የቻለበትን ግብ ፍሬው ሰለሞን በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ አክርሮ በመምታት አስቆጠረ ።

የጨዋታው መገባደጃ ደቂቃዎች ላይ በድሬደዋ ከተማ በኩል በማጥቃት ቦታ ላይ ቅያሪዎችን በማድረግ ግብ ለማስቆጠር ቢሞክሩም ያን ማድረግ ሳይችሉ ቀሩ ይባሱንም መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ በጭማሪ ደቂቃዎች ላይ ይገዙ ቦጋለ ለራሱ ሁለተኛውን ለክለቡ ደግሞ ሶስተኛውን ግብ አስቆጠረ ። ጨዋታውም በሲዳማ 3 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ ።

Writer at Hatricksport

Facebook

Habtamu Mitku

Writer at Hatricksport