“አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር ስለደበደበኝ ከቡድኑ አግጄዋለሁ ጥርሴም ተጎድቷል” አቶ ሲሳይ.ተረፈ /የአ/አከተማ እግርኳስ ቡድን መሪ/

አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር
ቡድኑን እንዳይመራ ታገደ….

*… ክለቡ 70 ሚሊየን ብር ተመድቦለታል..

“ውሸት ነው አልደበደብኩትም..ከዚህ ውጪ የምነግርህ ነገር ግን የለም”
አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር

የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ቡድን በአርባምንጭ ከተማ 2 ለ 1 በተረታበት ጨዋታ አሰልጣኙ እስማኤል አቡበከር ቡድኑን ያለመምራቱ ምክንያት አነጋጋሪ ሆኗል።

አሰልጣኙ ቡድኑን ያልመራው የቡድን መሪው ለአወዳዳሪው አካል ስሙን ስላላስተላለፈው መሆኑን ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ያስረዳል። በጉዳዳዩ ዙርያ የተጠየቀው የቡድን መሪው ሲሳይ ተረፈ እንደተናገረው” ስሙን ለአወዳዳሪ አካል አለማስተላለፌ እውነት ነው ህግና መንግስት ባለበት ደብድቦኝ ጥርሴን ጎድቶታል ስነምግባር ከሌለው ደግሞ ለቡድኑ አስተማሪ መሆን አይችልም” ሲል ተናግሯል።

ቡድን መሪው እንደገለጸው ” አለመግባባቱ የቆየ ነው እስካሁን መፍትሄ አላገኘም ልዩነቶች በውይይት ይፈታል እንጂ በሰለጠነ አለም ድብድብ አልጠበኩም ስለ ጉዳዩ ለጸጥታ ሃይል አሳውቄያለሁ በኛ በኩል ባለው ውሳኔ ስለደበደበኝ ከቡድኑ አግጄዋለሁ” ብሏል።

አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር በበኩሉ ” ውሸት ነው አልደበደብኩትም ከዚህ ውጪ የምነግርህ ነገር የለም” ሲል አስተባብሏል። የአሰልጣኙ ውል ጥቅምት 30/2014 ሊጠናቀቅ ሁለት ሳምንት ብቻ በቀረበት ሰአት አለመግባባቱ ወደ አካላዊ ንክኪ አድጓል መባሉ ቀጣዩን ጊዜ አጓጊ አድርጎታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክርቤት ለክለቡ የ70 ሚሊየን ብር በጀት መፍቀዱ ታውቋል። ይህም ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ ላይ እንዲቆይ ለሚደረገው ጥረት የማይናቅ አስተዋጽዎ እንደሚኖረው ይገመታል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport