መነሻ ገጽ ሉሲዎቹ የሉሲዎቹ አለቃ ብርሃኑ ግዛው የነገውን ጨዋታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል
ሉሲዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

የሉሲዎቹ አለቃ ብርሃኑ ግዛው የነገውን ጨዋታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል

አጋራ
አጋራ

 

“የተጨዋቾች ድርቅ አለብን”

” የማይገለበጥ ጨዋታ አይደለም የ2ለ0 ሽንፈቱን ገልብጠን እናልፋለን”

አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው

“የነበረብንን የአጨራረስ ድክመት እንደምናስተካክል ርግጠኛ ነኝ”

ሎዛ አበራ/የሉሲዎቹ አምበል/

ሉሲዎቹ ከኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ጋር ያላቸው
የመልስ ጨዋታ ነገ ከመካሄዱ በፊት ዛሬ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ስለጨዋታው መግለጫ ተሰጥቷል።

አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው በሰጡት መግለጫ
“ከኡጋንዳ ጋር ተጫውተን 2 ለ 0 በተሸነፍንበት ጨዋታ የመጀመሪያ 20 ደቂቃዎች ኳስ መጫወት አልቻልንም የስነ ልቦና የበላይነት ተወስዶብናል ግብ ሲቆጠር ቶሎ እርብሽብሽ የማለትና ያለማገገም ክፍተት ነበረብን ያንን ለማስተካከል ስንሰራ ቆይተናል አሁንም የማይለቀበስ ጨዋታ የለም እንኳን ሁለት ከዚያ በላይ ተቆጥሮም ተገልብጦ እንደሚያውቅ በመግለጽ ተጨዋቾቻችንን አበረታታናቸዋል”ሲሉ ገልጸዋል።

“የቡድኑ አባላት የጨዋታውን ሙሉ ቪዲዮ በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ለነገው ጨዋታ ዝግጁ ሆነናል በአጠቃላይም በነገው ጨዋታ የ2 ለ 0 ሽንፈቱን ገልብጠን እንደምናልፍ ርግጠኛ ነን። ኡጋንዳዎች በ2 አመት ቆይታ 12 ጨዋታ አድርገዋል እኛ ግን ውድድር ከተደረገ 8 ወር የወዳጅነት ጨዋታ ካደረግን 5 ወር ሞልቶናል” በማለት ተናግረዋል።

አሰልጣኙ እንደሚሉት “የወዳጅነት ጨዋታ በተመለከተ ከወንዶች ጋር ለመጫወት ተገደናል ሳይንሱም ፊፋም አይፈቅዱም ያው አማራጭ ስላጣን ያለውን ለመቀበል ተገደናል በርግጥም

ወንዶች ጉልበት ሴቶች ብልሃት እንዳላቸው መረሳት የለበትም በቀጣይ ግን መታረምና መስተካከል አለብን” ሲሉ ተናግረዋል።

አምበሏ ሎዛ አበራ በበኩሏ”እኔን ጨምሮ የአጨራረስ ድክመት ነበረብን የተገኘ ዕድል አልተጠቀምንም ከነገው ጨዋታ በፊት ደጋግመን ችግራችንን ስላየን በተሻለ የአጥቂ ክፍል ቅንጅት ውጤታማ እንደምንሆን ርግጠኛ ነኝ” በማለት አስተያየቷን ሰጥታለች። አሰልጣኙ አጽንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት “የተጨዋቾች ድርቅ አለብን ያንን ለማስወገድ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል” ሲሉም አሳስበዋል።

አሰልጣኝ ብርሃኑ አክለውም “ተጨዋቾቼ በመልካም ጤንነት መገኘታቸው በተሻለ አቅም ስህተታችንን ለማረም መቻላችንን ስናይ የነገውን ጨዋታ በርግጠኝነት እናሸንፋለን ውጤቱም የሚገለበጥም ነው’ በማለት ተናግረዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...