መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ | አፄዎቹ ከተከታታይ ነጥብ መጣል በኋላ ሲዳማ ቡናን በሰፊ ውጤት አሸንፈዋል
ሲዳማ ቡናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

የጨዋታ ዘገባ | አፄዎቹ ከተከታታይ ነጥብ መጣል በኋላ ሲዳማ ቡናን በሰፊ ውጤት አሸንፈዋል

አጋራ
አጋራ

በዕለቱ የተደረገው ሁለተኛ ጨዋታ ፋሲል ከተማን ከሲዳማ ቡና አገናኝቶ ፋሲል ከተማዎች በመጀመሪያዎቹ 18 ደቂቃዎች ባስቆጠሯቸው 3 ግቦች እና ከእረፍት መልስ በ47ኛ ደቂቃ በተቆጠሩ ግቦች 4 ለ 0 በማሸነፍ ከተከታታይ ነጥብ መጣል በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሰዋል ።

ፋሲል ከተማዎች በስድስተኛ ሳምንት ከወላይታ ድቻ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ከተጠቀሙት ቋሚ 11 ሶስት ቅያሪዎችን በማድረግ ያሬድ ባየህን ሳሙኤል ዮሀንስን እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ወደ ቋሚ አሰላለፍ ሲመልሱ ሲዳማ ቡናም ከአዳማ ከተማ አቻ በተለያየበት ጨዋታ ከነበሩት ቋሚ ተሰላፊዎች ሁለት ቅያሪ በማድረግ ሙሉአለም መስፍንን እና ምንተስኖት ከበደን ጨዋታውን እነፈንዲጀምሩ አድርገዋል ።

በፈጣን ግለት የተጀመረው ጨዋታ ግብ ያስተናገደው ገና በሶስተኛ ደቂቃ ላይ ነበር ። አምሳሉ ጥላሁን ያሻማውን የማዕዘን ምት የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ተክለማርያም ሻንቆ እና ግርማ በቀለ ባለመናበባቸው ምክንያት በተፈጠረ ስህተት ኳሱን ያገኘው አለምብርሀን ይግዛው አስቆጥሮ አፄዎቹን ቀዳሚ አደረገ ። ሲዳማ ቡናዎች ኳሱን ይዘው ከሜዳቸው ለመውጣት በሚያደርጉት ጥረት የሚቀሟቸው ኳሶች ፋሲል ከተማዎች በፈጣን መልሶ ማጥቃት ጫና እንዲፈጥሩባቸው አድርጎ ነበር ።


በዚህም 8ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጣሪው አለምብርሀን ይግዛው ከበረከት ደስታ የደረሰውን ኳስ ወደ ሳጥን ውስጥ ይዞ በመግባት ወደ ግብ ቢሞክረውም ግብ ጠባቂው መልሶበታል ።

በጨዋታው ከ16ኛ እስከ 18ኛ ደቂቃ ለፋሲል ከተማ የሀሴት ለሲዳማ ቡና ደግሞ የቅዠት ደቂቃዎች ነበሩ ። 16ኛው ደቂቃ ላይ ኦኪኪ አፎላቢ ወደ ኋላ ተመልሶ ያገኘውን ኳስ የሲዳማ ቡና ተከላካዮችን በመሸወድ በግራ መስመር ላይ ለነበረው በረከት ደስታ ያቀበለው ሲሆን በረከትም ጀርባውን ለግቡ ሰጥቶ የተቀበለውን ኳስ በኋላ እግሩ በፍጥነት ወደ ሳጥይ እየገባ ለነበረው አምሳሉ ጥላሁን አቀብሎት አምሳሉ ኳሱን አክርሮ በመምታት ለአፄዎቹ ሁለተኛውን ግብ አስቆጠረ ።

የፋሲል ከተማዎች የሁለተኛ ጎል ደስታ ሳይበርድ የሲዳማንፈ ቡና ተጫዋቾች ድንጋጤም እንዳለ ሌላ ግብ ተቆጠረ ። ኦኪኪ አፎላቢ ከበረከት ደስታ በግሩም ሁኔታ የደረሰውን ኳስ በሁለት የሲዳማ ቡና ተከላካዮች መሀል በማለፍ እና ኳሱን ተቆጣጥሮ በድንቅ አጨራረስ የአፄዎቹን ሶስተኛ ግብ በቀድሞ ክለቡ ላይ አስቆጠረ ።

ገና በጊዜ ሶስት ግቦችን ያስተናገዱት ሲዳማ ቡናዎች ኳስ ይዘው በቀላሉ ወደ ፋሲል ከተማ የግብ ክልል ለመድረስ ተቸግረዋል ። በአንፃሩ ፋሲል ከተማዎች በፍጥነት ወደ ግብ ይዘዋቸው የሚሄዱ ኳሶች ተጨማሪ ግብ ሊያስቆጥሩ እንደሚችሉ አመላካች ነበሩ ። በአጋማሹ በሲዳማ ቡና በኩል ሊጠቀስ የሚችለው ብቸኛ የግብ ሙከራ 22ኛው ደቂቃ ላይ የተደረገው ነበር ። ሀብታሙ ገዛኸኝ በረጅም የተላከለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ ተቆጣጥሮ ወደ ግብ የሞከረው ኳስ በሳሙኤል ሳማኪ ተመልሶበታል ። ከውሀ እረፍት በኋላ ሲዳማ ቡናዎች በተሻለ ለመንቀሳቀስ የሞከሩበት ሆኖ ያለፈ ሲሆን በ 3 ለ 0 ውጤት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቀቀ ።

የሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ልክ እንደመጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ ገና በጊዜ ነበር ግብ ያስተናገደው ። ፋሲል ከተማዎች በጥሩ አካሄድ ይዘው የሄዱትን ኳስ ሽመክት ጉግሳ በሳጥን ውስጥ ነፃ ሆኖ ለሚጠብቀው በረከት ደስታ በማቀበል የአፄዎቹ መሪነት ወደ 4 ለ 0 አደገ ።

ሲዳማ ቡናዎች ኳሱን ይዘው በተጋጣሚ ሜዳ በተደጋጋሚ መግባት ቢችሉም የፋሲል ከተማ የተከላካይ መስመርን ማለፍ ከባድ ሆኖባቸዋል ። በአንፃሩ ፋሲል ከተማዎች በፈጣን መልሶ ማጥቃቶች ከሚፈጥሯቸው የግብ ዕድሎች በተጨማሪ ኳሱን በመያዝ እና ወደ ኋላ መልሰውም በጥሩ ጨዋታ ወደ ፊት በመሄድ የጨዋታውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ችለዋል ።

የፋሲል ከተማ ተከላካዮችን ለማለፍ ያልቻሉት የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች በቴዎድሮስ ታፈሰ ፤ መሀሪ መና ፤ ይገዙ ቦጋለ አማካኝነት ከሳጥን ውጪ የሚያደርጓቸው የነበሩት የግብ ሙከራዎች ኢላማቸውን የጠበቁ አልነበሩም ። በአጋማሹ ብቸኛው በሲዳማ ቡና በኩል የተደረገው ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ 90+3 ላይ በይገዙ ቦጋለ የተደረገው ሲሆን ኳሱን ሚካኤል ሳማኪ በቀላሉ ይዞታል ።

በአፄዎቹ በኩልም አራተኛውን ግብ ካስቆጠሩ በኋላ ያደረጉት ብቸኛ ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ በ75ኛው ደቂቃ ላይ ሽመክት ጉግሳ ያሻገረውን ኳስ ኦኪኪ ሞክሮት ተክለማርያም የማዕዘን ምት ያደረገወሰ ኳስ ነበር ።
ጨዋታውም በስተመጨረሻ በአፄዎቹ የ4 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ ።

ውጤቱን ተከትሎም ፋሲል ከተማ ነጥቡን 15 በማድረስ የሊጉ አናት ላይ ሲቀመጥ ሲዳማ ቡና በነበረው 7 ነጥብ የሚቆይ ቢሆንም በተቆጠሩበት ግቦች ምክንያት ከ11ኛ ወደ 13ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...