By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ቡናማዎቹ ተከታታይ ሶስተኛ ድላቸውን ሲያስመዘግቡ ሀድያ ሆሳዕና ከሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችኢትዮ-ኤሌክትሪክሲዳማ ቡናሀዲያ ሆሳዕናየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቡናማዎቹ ተከታታይ ሶስተኛ ድላቸውን ሲያስመዘግቡ ሀድያ ሆሳዕና ከሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 1 year ago
Share
SHARE

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታድየም መደረግ ጀምረዋል።

የዕለቱ ቀዳሚ መርሐግብር በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ተደርጎ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል።

የቡናማዎቹን ብቸኛ ግብ ጋናዊው ኮንኮኒ ሀፍዝ በ18ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል። ኮንኮኒ ሀፍዝ ላስቆጠረው ግብ ኳሱን አመቻችቶ ያቀበለው አማካዩ ይታገሱ እንዳለ ነው።

የውድድር ዓመቱን አምስተኛ ግብ ያስቆጠረው ጋናዊው አጥቂ ባሳለለፍነው ሳምንትም ኢትዮጵያ ቡና ስሁል ሽረን ሲረታ ብቸኛውን ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል።

- ማሰታውቂያ -

ኢትዮጵያ ቡና በውድድር ዓመቱ ለ11ኛ ጨዋታ ግብ ሳያስተናግድ ያጠናቀቀበት ሲሆን ባለፉት አራት ተከታታይ ጨዋታዎችም የዳንላንድ ኢብራሂም መረብ አልተደፈረም።

የነፃነት ክብሬው ቡድን ነጥቡን 32 በማድረስም ከመሪው ኢትዮጵያ መድን ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ አድርጓል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በበኩሉ ከመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ አራት ጨዋታዎች በሶስቱ አሸንፎ የነበረ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ግን ተከታታይ ሽንፈት አስተናግዷል።

በ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ስሁል ሽረ በመጪው እሁድ የካቲት 30 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አመሻሽ 12:00 ጀምሮ በተደረገው ጨዋታ ደግሞ ሀድያ ሆሳዕና እና ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል።

በጨዋታው መስፍን ታፈሰ አሊቶዎቹን ገና በሶስተኛው ደቂቃ ላይ መሪ ማድረግ ቢችልም ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ እዮብ አለማየሁ ያስቆጠረው ግብ ከቤራዎቹን አቻ አድርጓል።

አስቀድሞ በመጀመሪያ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ ሁለት ግቦችን ያስተናገደው ጨዋታው በቀሪ ደቂቃዎች ግብ ሳያስተናግድ ተጠናቋል።

ለሳምንታት በመሪዎቹ ተርታ የሚገኘው ሀድያ ሆሳዕና ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ያሸነፈ ሲሆን ማግኘት ከሚችለው 18 ነጥቦች ማሳካት የቻለው 6 ብቻ ነው።

ሲዳማ ቡና በበኩሉ ተከታታይ ሶስተኛ የአቻ ውጤቱን ያስመዘገበ ሲሆን ሽረ እንደስላሴን ያሸነፈበት ጨዋታ ካለፉት ስምንት ጨዋታዎች ያስመዘገበው ብቸኛ ድሉ ነው።

ሀድያ ሆሳዕና ነጥቡን 32 ቢያደርስም ኢትዮ ኤሌክትሪክን በረታው ኢትዮጵያ ቡና በንፁህ ግቦች ተበልጦ 3ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ሲገደድ ሲዳማ ቡና ምንም እንኳን በነበረበት 11ኛ ደረጃ ቢቀጥልን ነጥቡን 25 አድርሷል።

በቀጣይ ሳምንት ጨዋታዎች ሀድያ ሆሳዕና ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከ አዳማ ከተማ የፊታችን ሰኞ መጋቢት 1 ቀን ይጫወታሉ።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የሃያኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Next Article አሊ ሱሌማን እና አህመድ ሁሴን ሀትሪክ በሰሩባቸው ጨዋታዎች ሐይቆቹ እና አዞዎቹ ጣፋጭ ድሎችን አሳክተዋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችThe BiG Interviewሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

የመጀመሪያዋ ባለቀለምና ተወዳጇ ሀትሪክ ሳምንታዊ የስፖርት ጋዜጣ በቅድሚያ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን፣ ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለች እንደተለመደው አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን አካታ በገና በዓል ምክንያት ከነገ በስቲያ ማለዳ እጅዎ ትገባለች ይጠብቋት።

hatricksport team By hatricksport team 6 years ago
ሀድያ ሆሳዕና ወሳኝ ተጨዋቾቹን ሊያጣ ነው
“እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አሰልጣኝ ሆኜ ሳይሆን በተጨዋችነት ሜዳ ውስጥ ግብጽን መፋለም እመርጥ ነበር” ኢንስትራክተር ዳንኤል ገ/ማሪያም / አዲሱ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ /
የጨዋታ ዘገባ | ድሬዳዋ ከተማ እና ስሑል ሽረ ነጥብ ተጋርተዋል።
“ግብፅን አሻግረን ማየት ጀምረናል”ብርሃኑ ግዛው የባንኮች አሰልጣኝ (ከኬንያ በተለይ ለሀትሪክ)
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?