የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ታምራት እያሱ(አርባምንጭ ከተማ) : ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ20ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 16 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. አቤል ሀብታሙ(ኢትዮ ኤሌትሪክ ) : ክለቡ ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው የ20ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 60 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ‥እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. ቃለአብ ውብሸት (ሀዲያ ሆሳዕና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ማሰታውቂያ -
ሀዲያ ሆሳዕና – ወላይታ ድቻ
ድሬደዋ ከተማ – ሀዲያ ሆሳዕና
ሀዲያ ሆሳዕና – ኢትዮጵያ መድን
ሀዲያ ሆሳዕና – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሃዋሳ ከተማ – ሀዲያ ሆሳዕና
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
4. ፍሬዘር ካሳ(ባህርዳር ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 9 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
ባህርዳር ከተማ – ሀዲያ ሆሳዕና
ኢትዮ ኤሌትሪክ-ባህርዳር ከተማ
ባህርዳር ከተማ – ሲዳማ ቡና
ስሁል ሽሬ – ባህርዳር ከተማ
መቐለ 70 እንደርታ -ባህርዳር ከተማ
ባህርዳር ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2000 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
4. አርባምንጭ ከተማ ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ20 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የአርባምንጭ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 ታምራት እያሱ
2 ታምራት እያሱ
3 ፍቃዱ መኮንን
4ይሁን እንዳሻው
5 ኢድሪስ ኦጎዶጆ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
5. አዳማ ከተማ ክለቡ ከኢትዮ ኤሌትሪክጋር በነበረው የ20ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ግጥሚያው 4 ደቂቃ ዘግይቶ ለመጀመሩ ምክኒያት እንደነበረ ሪፖርት
ቀርቦበታል ።
በመሆኑም በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 ተቁ 17 መሰረት ከለቡ ብር 15000/አስራ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


