By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: አዞዎቹ እና ነብሮቹ ከአስደናቂ ጨዋታ በኋላ ነጥብ ሲጋሩ የጦና ንቦቹ ወደ ድል ተመልሰዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ
ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሲዳማ ቡና
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችአርባምንጭ ከተማመቐለ 70 እንደርታሀዲያ ሆሳዕናየጨዋታ ዘገባ

አዞዎቹ እና ነብሮቹ ከአስደናቂ ጨዋታ በኋላ ነጥብ ሲጋሩ የጦና ንቦቹ ወደ ድል ተመልሰዋል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 1 year ago
Share
SHARE

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ሲደረጉ ከአመሻሽ 12:00 ጀምሮ የተደረገው የአርባምንጭ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ 3 – 3 ተጠናቋል።

በጨዋታው ሀድያ ሆሳዕናዎቹ ገና በጊዜ 2 – 0 መሪ መሆን ነበር።

በ4ኛው ደቂቃ ላይ ሄኖክ አርፊጮ ከቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ የመታው ኳስ በቀጥታ የሀድያ ሆሳዕና መረብ ላይ አርፏል።

በ14ኛው ደቂቃ ደግሞ ዳግም ንጉሴ ከማዕዘን የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር የከቤራዎቹን መሪነት ወደ 2 – 0 ከፍ አድርጓል።

- ማሰታውቂያ -

በ26ኛው ደቂቃ ላይ ዳግም ንጉሴ በአህብዋ ብሪያን ላይ በሳጥን ውስጥ የሰራውን ጥፋት ተከትሎ አዞዎቹ የፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኙም ጥፋቱ የተሰራበት ብሪያን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ወቅት ግን አዞዎቹ ወደ ጨዋታው የመለሳቸውን ግብ ከመረብ አሳርፈዋል።

በ45+3 ደቂቃ ላይ ከአርባምንጭ የቀኝ አቅጣጫ ወደ ሳጥኑ የተሻገረውን ኳስ ቡታቃ ሸመና በደረቱ አረጋግቶ የሀድያ ሆሳዕናውን ግብ ጠባቂ ያሬድ በቀለ ስህተትም ታክሎበት ግቡን አስቆጥሯል።

በርካታ ክስተቶችን እያስመለከተ በቀጠለው ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽም ተጨማሪ ግቦችን አክሏል።

በ60ኛው ደቂቃ ላይ የፍፁም ቅጣት ምቱን መጠቀም ያልቻለው አህባዋ ብሪያን በረጅም የተላከለትን ኳስ የያሬድ በቀለን ሁለተኛ የጊዜ አጠባበቅ ስህተት ተጠቅሞ አርባምንጭ ከተማን አቻ አድርጓል።

ከግቡ መቆጠር ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ግን አዞዎቹ አንድ ተጫዋች በቀይ ካርድ ማጣታቸውን ተከትሎ ቀሪውን ደቂቃ በ10 ተጫዋቾች ለመጨረስ ተገደዋል።

ተከላካዩ አሸናፊ ፊዳ ከኳስ ውጪ በሆነ እንቅስቃሴ እዮብ አለማየሁ ላይ የመታው ሲሆን በቅርበት ሆነው ሁነቱን የተመለከቱት የዕለቱ ዋና ዳኛ በቀጥታ የቀይ ካርድ ከሜዳ አስወግደውታል።

ጨዋታው 75ኛ ደቂቃ ላይ በደረሰበት ወቅት ግኑ አርባምንጭ ከተማዎች 2 – 0 ሲመሩበት የነበረውን የጨዋታ ውጤት ወደ 3 – 2 መቀየር የቻሉበትን ግብ አስቆጥረዋል።

ይሁን እንደሻው ከቆመ ኳስ ወደ ግብ ክልል ያሻገረውን ኳስ ቡታቃ ሸመና በጭንቅላት ገጭቶ በማስቆጠር የአዞዎቹን ደጋፊዎች አስፈንድቋል።

ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ አሸናፊነት የተጠናቀቀ በመሰለበት የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ ግን ጫና ፈጥረው የነበሩት ከቤራዎቹ 3 – 3 የሆኑበትን ግብ በብሩክ ማርቆስ አማካይነት አግኝተዋል።

በመጨረሻም ጥሩ ፉክክር እና በርካታ ክስተቶች የነበረው ጨዋታ በሶስት አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን ውጤቱንም ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና ነጥቡን 27 ሲያደርስ አርባምንጭ ከተማ በበኩሉ ነጥቡን 24 አድርሷል።

በ19ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሀድያ ሆሳዕና ከቅዱስ ጊዮርጊስ አርባምንጭ ከተማ ደግሞ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ይገናኛሉ።

በዕለቱ በቀዳሚነት በተደረገው ጨዋታ ወላይታ ድቻ መቀሌ 70 እንደርታን አሸንፏል።

እምብዛም ሳቢ ባልነበረው ጨዋታ ካርሎስ ዳምጠው በ73ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ግብ ለጦና ንቦቹ ሶስት ነጥብ ማሳካት በቂ ነበረ።

ካርሎስ ዛሬ ያስቆጠረውን ግብ ተከትሎም በውድድር ዓመቱ በሊጉ ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛቶች 4 ማድረስ ችሏል።

ድሉ ለወላይታ ድቻ ከተከታታይ ሶስት ድል አልባ እና ሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ የተገኘ ሲሆን መቀሌ 70 እንደርታ በበኩሉ ሊጉ አዳማ ላይ መካሄድ ከጀመረ በኋላ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በቀጣይ ሳምንት መርሐግብር ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲጫወት መቀሌ 70 እንደርታ አራፊ ቡድን ነው።

You Might Also Like

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ቅዱስ ጊዮርጊስ የዳኝነት በደል ደርሶብኛል በማለት ቅሬታውን አቀረበ
Next Article አንዋር ሙራድ ለአሰልጣኙ ውድ የልደት ስጦታ ሲያበረክት ሻምፕየኑ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ከተማን ረቷል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዲስአበባ ከተማወልቂጤ ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | ወልቂጤ ከተማ በጌታነህ ከበደ ብቸኛ ግብ ሶስት ነጥብ አግኝቷል

Habtamu Mitku By Habtamu Mitku 4 years ago
የክልል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች  የተጨዋቾን ዝውውር እንዳያጸድቁ ተከለከለ
የጨዋታ ዘገባ | የፍሬዘር ካሳ ግብ ሀድያ ሆሳዕናን አሸናፊ አድርጓል
ዜና | በካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ወላይታ ድቻ እና ቅ/ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸው ታወቁ።
ፊሊፕ ኦቮኖ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ለመቀጠል ተስማምቷል
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?