By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: መድኅን መሪነቱን ሲያጠናክር መቀሌ 70 እንደርታም ድል ቀንቶታል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችአዳማ ከተማመቐለ 70 እንደርታየጨዋታ ዘገባኢትዮጵያ መድህን

መድኅን መሪነቱን ሲያጠናክር መቀሌ 70 እንደርታም ድል ቀንቶታል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 1 year ago
Share
SHARE

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም በሁለተኛ ቀን መርሐግብር ቀጥለው ሁለት ጨዋታዎች በአ.ሳ.ቴ.ዩ. ስታድየም ተደርገዋል።

አመሻሽ 12:00 ጀምሮ የተደረገው እና በብዙ የተጠበቀው የኢትዮጵያ መድኅን እና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ በኢትዮጵያ መድኅን የ1 – 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ ስድስት ያህል ደቂቃዎች ሲቀሩት የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወልቂጤ ከተማ ተጫዋች አቡበከር ሳኒ መድኅንን አሸናፊ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል።

የገብረመድህን ኃይሌው ቡድን ተከታታይ 5ኛ ድሉን በማስመዝገብ መሪነቱን ሲያጠናክር በውድድር ዘመኑ አስረኛ ግብ ያላስተናገደበት ጨዋታ ሆኗል።

- ማሰታውቂያ -

ኢትዮጵያ መድኅን ዘንድሮ በአንድ ጨዋታ ብቻ ሽንፈት ያስተናገደ ብቸኛው ቡድን ሲሆን የሊጉን መሪነት ተከታዮቹ እስኪጫወቱ በሶስት ነጥቦች መራቅ ችሏል።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታድየም ከአስራ ሶስት ጨዋታዎች በኋላ የተረታው ኢትዮጵያ ቡና ሊጉ ወደ አዳማ ካቀና በኋላ ያላስደፈረው መረቡ ዛሬ ግብ አስተናግዶ ለመሸነፍ ተገዷል።

በ16ኛ ስምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ ቡና ባህርዳር ከተማን ሲገጥም ኢትዮጵያ መድኅን በበኩሉ ከሀድያ ሆሳዕና ይጫወታል

ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ በተደረገው የዕለቱ ቀዳሚ መርሐግብር መቀሌ 70 እንደርታ በከተማው የሚጫወተውን አዳማ ከተማን 2 – 0 ረቷል።

በጨዋታው አራተኛ ደቂቃ ላይ በመጀመሪያ ሳምንታት በተከታታይ ጨዋታዎች ግብ በማስቆጠር ላይ የነበረው ያሬድ ብርሀኑ ከግብ ጋር ታርቆ ቡድኑን መሪ አድርጓል።

ተጫዋቹ ረጅም ሜትሮችን እየገፋ የሄደውን ኳስ በሳጥኑ የግራ አቅጣጫ ይዞ በመግባት እና በግራ እግሩ በመምታት ኳስ እና መረብን አገናኝቷል።

የሁለተኛው አጋማሽ በተጀመረ 87ኛው ሰከንድ ላይ ደግሞ የዳንኤል ፀሐዬው ቡድን ዳግም መሪ የሆነበትን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

በቡድኑ ሁለተኛ ጨዋታውን ያደረገው ሔኖክ አዱኛ ከቆመ ኳስ ወደ ግብ ክልል ያሻገረውን ኳስ ቤንጃሚን ኮቴ በግንባር በመግጨት ኳስ እና መረብን አዋህዷል።

ውጤቱንም ተከትሎ መቀሌ 70 እንደርታ ነጥቡን 21 በማድረስ በጊዜያዊነት 7ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን አዳማ ከተማ በበኩሉ ሽንፈቱን ተከትሎ 15ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ የወራጅ ቀጠናውን ተቀላቅሏል።

በቀጣይ ሳምንት መርሐግብር መቀሌ 70 እንደርታ ከአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይጫወታሉ።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article አህመድ ሁሴን አዞዎቹን ባለ ድል ሲያደርግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከስሁል ሽረ ነጥብ ተጋርቷል
Next Article ጋቶች ፓኖም በአዲሱ ክለቡ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎችCovid-19

ለባለውለተኞቻችን የተዘረጋው የሸዋረጋ ደስታ እና የጓደኞቹ ደጋግ እጆች

Yishak belay By Yishak belay 6 years ago
የጨዋታ ዘገባ | መቻል የሊጉን መሪ ማሸነፍ ችሏል
“ስሜን በሀሰት አጉድፈው የቤተሰቤንና የወዳጆቼን አንገት ያስደፉትን በፍትህ አደባባይ ለመፋረድ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ”ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው
ወጣቱ የግብ ዘብ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል!!
ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ጃፋር ደሊልን አስፈረመ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?