ጋቶች ፓኖም በአዲሱ ክለቡ ኒውሮዝ የመጀመሪያ ግቡን ምሽቱን በተደረገ ጨዋታ በወሳኝ ሰዓት ላይ አስቆጥሯል።
የጋቶች ቡድን ኒውሮዝ ከሜዳው ውጪ ሾርታ የተሰኘውን ክለብ በገጠመበት ጨዋታ እስከ 99ኛ ደቃቃ ድረስ 2 – 1 እየተመራ ቢቆይም በ90+10 ደቂቃ ላይ ኢትዮጵያዊው ተጫዋት በግንባር ገጭቶ ባስቆጠረው ግብ ከሸንፈት ድኗል።
ሾርታ ክለብ ይህን ጨዋታ አሸንፎ ቢሆን ኖሮ የሊጉ መሪ መሆን ይችል ነበር።
ጋቶች ቡድኑን ከተቀላቀለ በኋላ ያደረገው ሶስተኛ ጨዋታውን ሲሆን በሶስቱም ሙሉ ደቂቃዎችን ተጫውቷል።
- ማሰታውቂያ -



