መነሻ ገጽ ዜናዎች ሽረ ከስምንት ጨዋታ በኋላ ድል ሲቀናው ንግድ ባንክ እና አርባምንጭም አሸንፈዋል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሽረ ከስምንት ጨዋታ በኋላ ድል ሲቀናው ንግድ ባንክ እና አርባምንጭም አሸንፈዋል

አጋራ
አጋራ

በሊጉ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ምድረገነት ሽረ ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል ሲመለሱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አርባምንጭ ከተማም ጣፋጭ ነጥብን ወደ ካዝናቸው ከተዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለቱን የመዲናይቱን ክለቦች ያገናኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ጎሎች የተቆጠሩበት በሁለተኛው አጋማሽ ሲሆን የድል ቁልፉን ያገኙትም ሀምራዊ ለባሾቹ ሆነዋል። 54ኛው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን ምት ተስፋዬ ታምራት ያሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ናትናኤል ዳንኤል ወደ ጎልነት ለውጦ የአሰሎጣኝ በፀሎት ልዑልሰገዱን ቡድን ቀዳሚ ማድረግ ሲችል ከአራት ደቂቃዎች በኋላ የአመቱን ዘጠኝ ጎል ከመረብ ደግሞ ማስቆጠር ችሏል።

58ኛው ደቂቃ ላይ ከመጀመሪያው አጋማሽ በተቃራኒው የተሰጠውን የማዕዘን ምት ናትናኤል በግንባር ገጭቶ ከመረብ በማሳረፍ ለራሱም ለቡድኑም ሁለተኛ ጎል በማድረግ ጨዋታው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ለ0 አሸናፊነት ተቋጭቷል።

ሌላኛው በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለቱን በወራጅ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ተያይዘው የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታን ከአርባምንጭ ከተማ ያገናኘው መርሀግብር አዞዎቹን ባለ ድል ያደረገ ወሳኝ ውጤት ተመዝግቦላታል። 14ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ ይገዙ ወደ መሐል የሰጠውን ኳስ ማማዱ ሴክ በድጋሚ አሾልኮ ሰጥቶት ይገዙ ወደ ጎል ሞክሮ የግብ ዘቡ መሐመድ ዛጉዬ ሲመልሳት የተመለሰችዋን ኳስ ያገኘው ጋናዊው አጥቂ መረቡ ላይ በማሳረፍ ቡድኑን መሪ አድርጓል።

በተሻለ ፍላጎት ከመጀመሪያው አጋማሽ የቀጠለው የአርባምንጭ ከተማዎች እንቅስቃሴ 87ኛው ደቂቃ ላይ ሌላ ጎል እንዲያገኙ ሆኗል። ኤፍሬም ታምራት ከማዕዘን ምት ከበፍቅር ግዛቸው ጋር ተቀባብሎ ወደ ውስጥ ሲያሻማ ከጉዳት ተመልሶ አካሉ አትሞን ተክቶ የገባው አሸናፊ ፊዳ በግንባር ጨርፎ ጎል በማድረግ ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማዎች 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሌላኛው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዳየም ላይ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡናን አገናኝቶ የነበረው ጨዋታ ምንም ጎል ሳይቆጠርበት 0ለ0 መጠናቀቅ ችሏል።

ማምሻውን በአዳማ የተደረገው ጨዋታ የምድረገነት ሽረ እና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ የአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬውን ምድረገነት ሽረን ከስምንት ድል አልባ ጉዞ በኋላ ከናፈቃቸው አሸናፊነት ጋር አገናኝቷቸዋል። 21ኛው ደቂቃ ላይ ከሜዳው የግራ የማጥቂያ ክፍል ከቅጣት ምት አምበሉ በሀይሉ ግርማ ያሻማውን ኳስ ዳንኤል ዳርጌ በጥሩ ዕይታ አመቻችቶ ሰጥቶት ከጉዳት መልስ ወደ ሜዳ የተመለሰው ተከላካዩ አንተነህ ተስፋዬ ተንሸራቶ መረቡ ላይ አሳርፎ ጨዋታው በምድረገነት ሽረ 1ለ0 ድል አድራጊነት ተፈፅሟል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...