By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ቡናማዎቹ ጦሩን ሲረቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዓመቱ ለሶስተኛ ጊዜ አሸንፏል
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችኢትዮጵያ ንግድ ባንክየጨዋታ ዘገባኢትዮጵያ መድህንመቻል

ቡናማዎቹ ጦሩን ሲረቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዓመቱ ለሶስተኛ ጊዜ አሸንፏል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 2 months ago
Share
SHARE

ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቻቸውን ረተዋል

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ሲደረጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጬሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።

በአዲስ አበባ ስታድየም በተካሄደው እና የአሰልጣኝ ለውጥ አድርጎ በምክትል አሰልጣኙ እየተመራ የቀረበውን ኢትየጵያ ቡና ከመቻል ያገናኘው ጨዋታ በቡናማዎቹ የ1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በመጀመሪያዎቹ 30 ደቂቃዎች ላይ የሙሉጌታ ምህረቱ መቻል ጫና በመፍጠር ደጋግሞ ወደ ኢትዮጵያ ቡና የግብ ክልል ለመድረስ ጥረቶችን አድርጓል።

- ማሰታውቂያ -

የመቻል ተደጋጋሚ የማጥቃት እንቅስቃሴ ጠንከር ባለ የግብ ሙከራዎች ለመታጀብ እስከ 23ኛው ደቂቃ መጠበቅ የግድ ብሎ ነበር።

በተጠቀሰው ደቂቃ ላይ ፈቱዲን ጀማል ከማዕዘን የተሻገረን ኳስ በግንባር በመግጨት ያደረገው ሙከራ ግብ ጠባቂውን ቢያልፍም ናትናኤል ፍሬው ኳሱን አውጥቶታል።

በተመሳሳይ በ29ኛው ደቂቃ ላይም ከማዕዘን በተሻገረ ኳስ ታውላ ቴዎፎል በግንባር ገጭቶ ያደረገውን ሙከራ ሚኪያስ ፀጋዬ አውጥቶታል።

ከጨዋታውን መጀመር ግማሽ ሰዓት በኋላ ወደ መቻል የግብ ክልል በአደገኛ አጋጣሚዎች መድረስ የቻሉት ቡናማዎቹ በ33ኛው ደቂቃ ላይ በዘላለም አባተ አማካይነት ያደረጉት ሙከራ በግቡ አግዳሚ ተመልሷል።

የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሊጠናቀቅ አንድ ደቂቃ ብቻ ሲቀረውን ግን ኢትዮጵያ ቡናዎች ግብ አግኝተዋል።

የአቡበከር አዳሙ ድንቅ ብቃት በታየበት እንቅስቃሴ ሁለት የመቻል ተከላካዮች አልፎ በመሄድ ለዲቫይን ዋቹኩዋ ያቀበለው ኳስ ከመረብ ላይ አርፏል።

በሁለተኛው አጋማሽ መቻሎች የአቻነቱን ግብ ለማግኘት ደጋግመው ወደ ቡናማዎቹ ሳጥን መድረስ ቢችሉም ኳስን እና መረብን ማገናኘት ዳገት ሆኖባቸዋል።

በ52ኛው ደቂቃ ላይ አብድልከሪም ወርቁ እንዲሁም ቸርነት ጉግሳ በ72ኛው ደቂቃ ላይ ያደረጓቸው ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች በእንዳሻው እሸቴ በቀላሉ ተይዘዋል።

መነሻቸውን ከመስመር ባደረጉ ኳሶች ተደጋጋሚ የማጥቃት አጋጣሚዎችን ለመፍጠር የሞከሩት መቻሎች ይህን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ሁለቱንም የመስመር ተከላካዮች በመቀየር ጭምር ግብ ለማስቆጠር ጥረዋል።

በኢትዮጵያ ቡና በኩል ከኳስ ጀርባ በቁጥር በዝተው በመገኘት የሚነጠቁ ኳሶችን በፈጣን ሽግግር እና በረጃጅም ኳሶች ተጨማሪ ግቦች ለማስቆጠር ሞክረዋል።

በተለይም በ84ኛው ደቂቃ ላይ አራት የቡናማዎቹ ተጫዋቾች ከሁለት የመቻል ተጫዋቾች ጋር ተገናኝተው ሳይጠቀሙበት የቀረው ዕድል አስቆጪ ነበር።

ግለት በነበረው የጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ መቻሎች በተለይም በ86ኛው ደቂቃ ላይ በቸርነት ጉግሳ እና አብዱልከሪም ወርቁ ያደረጓቸው ሙከራዎች በኢትዮጵያ ቡና ተከላካዮች ተመልሰዋል።

ውጤቱንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 15 ያደረሰ ሲሆን መቻል በበኩሉ በ20 ነጥብ ላይ ለመቆየት ተገዷል።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታድየም የ2016 እና የ2017 ሻምፒዮኖቹን ባገናኘው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ መድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በጨዋታው የረመዳን የሱፍ የ22ኛ ደቂቃ ግብ ኢትዮጵያ መድንን እስከ 50ኛው ደቂቃ ድረስ መሪ አድርጎ ነበር።

ነገር ግን በሁለተኛው አጋማሽ ናትናኤል ዳንኤል በ51ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥሮ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አቻ አድርጓል።

ከ11 ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ አምበሉ አዲስ ግደይ ያስቆጠረው ግብ የበፀሎት ልዑልሰገዱን ቡድን አሸናፊ አድርጓል።

ውጤቱንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥቡን 15 ሲያደርስ ኢትዮጵያ መድን በበኩሉ 13 ነጥብ ላይ ለመቆየት ተገዷል።

በ13ኛው ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና ከምድረ ገነት ሽረ እንዲሁም መቻል ከነገሌ አርሲ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ነገሌ አርሲ 19 ነጥብ ላይ የደረሰበትን ድል ሲያስመዘግብ አዳማ ከተማ የውድድር ዘመኑን 5ኛ ድል አሳክቷል
Next Article የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮከቡ ከወራቶች ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ ተመልሷል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ETHEPLEnglish Article

Tsegaye KidaneMariam appointed Hadiya Hosaena head coach

Teshome Fantahun By Teshome Fantahun 6 years ago
የ2011 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች በቀጥታ ውጤት /LIVESCORE/ ይከታተሉ
“ቅዱስ ጊዮርጊስ የሲቲ ካፑን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ትላልቅ ዋንጫዎች ጠራርጎ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል” የአብስራ ተስፋዬ (ቅ/ጊዮርጊስ)
” መንግስት ከጠየቅነዉ 51 ሚሊየን ብር 35 ሚሊየኑን ሰጥቶናል” የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን
የአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያካሂዳሉ !
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?