በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ አዲስ አበባ የመጨረሻ ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡናን ከ አዳማ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ አዳማ ከተማ በ 56 ደቂቃ ነቢል ኑረዲን ባስቆጠራት ጎል ማሸነፍ ችሏል !
በመጀመሪያ አጋማሽ ብዙም ሳቢ ባለነበረው የጨዋታ አዳማዎች በተደጋጋሚ ወደ ጎል መድረስ ቢችሉም ለጎል የቀረበ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም
በሁለተኛው አጋማሽም ኢትዮጵያ ቡናዎች የተወሰደባቸውን ብልጫ ለመመል አዳማ ከተማ ጎል ለማስቆጠር ሙከራ ሲደርጉ ተስተውሏል ።

- ማሰታውቂያ -
አዳማዎች የኢትዮጵያ ቡና የሆነው ኦካይ ጁል የሰራውን ስህተት በመጠቀም በነቢል ኑረዲን አማካኝነት የአሸናፊነት ጎል ማግኘት ችለዋል
ከ ጎል በዋኃላ ቡናዎች ብልጫ ለመውሰድ መሀል ክፍሉን ሙሉ በሙሉ ለውጥ ማድረግ የቻሉ ቢሆንም ሳይሳካላቸው ቀርቷል በተለይም ተቀይሮ የገባው የፊት አጥቂዎ ሀብታሙ አሸናፊ ለጎል የቀረበ ሙከራ ማድረግ ቢችልም ሳይሳካለት ቀርቷል

በጨዋታው የኢትዮጵያ ቡና የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች የሆነው በፍቃዱ አለማየሁ ከ መሀል ዳኛ ሀይማኖቱ ወርቁ ጋር እሰጣገባውስ በመግባት ከሜዳ ተውግዷል
አዳማ ከተማ አዲስ አበባ ላይ ያደረጋቸውን አምስት ጨዋታ ሳይሸነፍ ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን የቡድኑ ግብ ጠባቂ አላዛር ማርቆስ በዘንድሮ የውድድር ዘመን በ አምስት ጨዋታዎች ጎል ሳይቀጠርበት ያጠናቀቀም ብቻኛ ግብ ጠባቂ መሆን ችሏል ።
የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ በሆነው የሸገር ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታ ሁለት ጎሎች ተቆጥረዋል !
ሸገር ከተማ በአራተኛው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስን በማሸነፍ ወደዚህኛው ጨዋታ የመጣ ሲሆን ሀዲያ ሆሳዕና በአንፃሩ በ መድን ተሸነፎ መምጣት ችሏል
በጨዋታው በሁለቱም በኩል ጥሩ እንቅስቃሴ የተደረገበት ሲሆን በጨዋታ የመጀመሪያውን አጋማሽ ሸገር ከተማዎች ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ የቻሉ ሲሆን በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ያሬድ በተደጋጋሚ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና መድረስ ችሏል በጨዋታው የሀዲያ ሆሳዕና ተከላካይ መስመር ዳግም ጥፋት በመስራቱ የፍፁም ቅጣት ምት የተሰጠ ሲሆን ሄኖክ አዱኛ ወደ ጎልነት መቀየር ችሏል ።

በመጀመሪያው አጋማሽ ያሬድ ግልፅ የጎል እድል ቢያገኝም ሳይጠቀም የቀረበት አጋጣም ለሸገር ከተማዎች የሚያስቆጭ ነበር
ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ሊጠናቀቅ ሽርፍራፊ ሰከንዶች በቀሩበት አጋጣም በሩክ በየነ ሀዲያ ሆሳዕናዎችን አቻ ማድረግ ችሏል
በሁለተኛ አጋማሽ እዚህ ግባ ሚባሉ ሙከራዎች ባይታዩበትም ለተመልካች ሳቢ ጨዋታ በማሳይት በ አቻ ጨዋታው ተጠናቋል


