ሸገር ከተማን ከገጠመበት ስብስብ አምስት ተጨዋቾች መቀየር የቻሉት ፈረሰኛዎቹ የጣና ሞገዶቹን ሶስት ለ አንድ አሸነፉ
ባህር ዳር ከተማ 1-3 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጨዋታው በጀመረ በ 2ተኛ ደቂቃ የባህርዳር ከተማ ግብ ጠባቂ የሆነው ይገርማል መኳንንት የሰራውን ጠፋት በመጠቀም ተገኑ ያሻገረለት ኳስ አቤል ያል በአስደናቂ አጨራረስ ማስቆጠር ችሏል ።
ቅዱስ ጊዮርጊስዎች ጫና በመፍጠር ሁለተኛ ጎል አቤል ያለው 26 ደቂቃ የተከላካዮችን ስህተት በመጠቀም ማስቆጠር ችሏል ።
- ማሰታውቂያ -

በጨዋታው ብልጫ ተወስዶባቸው የነበሩት ባህርዳሮች በ 32 ደቂቃ በረከት ጥጋቡ ከ ሳጥን ውጭ አክርሮ በመታው ኳስ ሁለት ለ አንድ መሆን የቻሉ ቢሆንም እረፍት ሊወጡ ሽርፍራፊ ሰከንዶች ሲቀሩት አዲሱ አቱላ ከ ሀብታሙ ጉላላት የተቀበለውን ኳስ ከ እርቀት በረኛው መውጣቱን ተመልክቶ አክርሮ በመምታት ማስቆጠር ችሏል ።

በሁለተኛ አጋማሽ ከመጀመሪያው አጋማሽ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስሶች በመጀመሪያ አጋማሽ የገኙትን ነጥብ አስጠብቀው ለመጫወት ሲሞክሩ ተስተውሏል ።
የእለቱ ሁለተኛ በሆነው ጨዋታ አዞዎቹ ከ አምና ሻምፒዮዎቹ ጋር ነጥብ ተጋርተዋል !!
ኢትዮጵያ መድን 0-0 አርባምንጭ ከተማ
በሁለቱም ቡድኖች በኩል የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ የተደረገበት ጨወታ ሲሆን ጨዋታው ያለግብ ባዶ ለባዶ መጠናቀቅ ችሏል
በጨዋታው የኢትዮጵያ መድን ተጨዋች የሆነው ረመዳን የሱፍ ለጎል የቀረበ ሙከራ ካደረገበት አጋጣሚ ውጪ በመጀመሪያው አጋማሽ የተለየ ሙከራ ያልተደረገ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ በተመሳሳይ ቀዝቃዛ እንቅስቃሴ ተደርጎበታል በሁለተኛው አጋማሽ አርባምንጭ ይሁን እንዳሻውን በ ሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ የተወገደባቸው ቢሆን ከ ሻምፒናዎቹ ነጥብ መጋራት ችለዋል



