By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ኢትዮጵያ መድን ወደ አሸናፊነት ሲመለስ መቻል ከማሸነፍ ጋር ተኳርፎ ቀጥሏል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ድሬዳዋ ከተማየጨዋታ ዘገባኢትዮጵያ መድህንመቻልየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግወልዋሎዜናዎች

ኢትዮጵያ መድን ወደ አሸናፊነት ሲመለስ መቻል ከማሸነፍ ጋር ተኳርፎ ቀጥሏል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 12 months ago
Share
SHARE

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች በዕለቱ ሲደረጉ በቀዳሚው ጨዋታ መቻል እና ወልዋሎ አዲግራት ነጥብ ተጋርተዋል።

ሁለቱ ከድል የተራራቁ ክለቦችን ባገናኘው ጨዋታ የላቀ የስብስብ ጥራት የያዘው መቻል በኳስ ቁጥጥሩ እና ወደ ተጋጣሚው የግብ ክልል ከመድረስ አንፃር የተሻለ ነበር።

ነገር ግን ከፊት መስመር ላይ ኳስና መረብን የሚያገናኝለት ተጫዋች ሳያገኝ ጨዋታውን አጠናቋል።

በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚመራው ቡድኑ ሊጉ የድሬደዋ ቆይታውን ሲያጠናቅቅ እና ወደ አዳማ ሲመጣ በመሪነት ላይ ተቀምጦ ነበር።

- ማሰታውቂያ -

ነገር ግን በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታድየም ላይ ካደረጋቸው ዘጠኝ ተከታታይ ጨዋታዎች በአንዱ(ስሁል ሽረን) ብቻ ነው ያሸነፈው።

መቻል አዳማ ላይ ማግኘት ከሚገባው 27 ነጥቦች ማሳካት የቻለው ስምንቱን ብቻ ነው። በደረጃ ሰንጠረዡም በ29 ነጥቦች 7ኛ ላይ ሆኖ ሳምንቱን አጠናቋል።

የሊጉን ግርጌ ይዞ ለበርካታ ሳምንታት በመዝለቅ ላይ ያለው ወልዋሎ አዲግራት የውድድር ዓመቱን ስድስተኛ የአቻ ውጤት አስመዝግቧል።

ቡድኑ ባለፉት ሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ከአንድ በላይ ግብ የማያስተናግድ ቢሆንም በተመሳሳይ የአጥቂ ክፍሉም በጨዋታ ከአንድ በላይ ግብ ማስቆጠር አልቻለም።

ከመጀመሪያ 12 የሊጉ ጨዋታዎች በ11 ተሸንፎ የነበረው ወልዋሎ አዲግራት ካለፉት ሰባት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ሽንፈት ያስተናገደው።

አሁንም ከ18ኛ ደረጃ መላቀቅ ባይችልም ነጥቡን ግን ዘጠኝ አድርሷል።

በቀጣይ ሳምንት መርሐግብር መቻል ከፋሲል ከነማ ወልዋሎ አዲግራት ደግሞ ከወላይታ ድቻ ይገናኛሉ።

ከአመሻሽ 12:00 ጀምሮ በተደረገው ጨዋታ ደግሞ ባሳለፍነው ሳምንት በወላይታ ድቻ የተረታው መሪው ኢትዮጵያ መድን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በጨዋታው መሀመድ አበራ ከበረከት ካሌብ ከቀኝ መስመር አቅጣጫ የተሻገረለትን ኳስ በማስቆጠር ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል።

መሐመድ ዛሬ ያስቆጠረውን ግብ ተከትሎ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛቶች 6 ማድረስ አስችሎታል።

መድን ማሸነፉን ተከትሎም ነጥቡን 38 በማድረስ ከተከታዩ ኢትዮጵያ ቡና ያለውን ልዩነት ወደ ስድስት አስፍቷል።

የአዳማ ቆይታው መልካም ያልሆነው ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉ ከድል ጋር ከተራራቀ አስር ጨዋታዎች ተቆጥረዋል።

የይታገሱ እንዳለው ቡድን አዳማ ላይ ካደረጋቸው ዘጠኝ የሊጉ ጨዋታዎችም በአምስቱ ነጥብ ሲጋራ በአራቱ ተሸንፏል።

ቡድኑ ከደረጃ ሰንጠረዡ በሁለት ነጥቦች ብቻ ርቆ በ21 የነጥብ ብዛቶች 14ኛ ላይ ተቀምጧል።

በ22ኛ ሳምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይገጥማሉ።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ በታንዛኒያ የመጀመሪያ ዋንጫዋን አሳካች
Next Article ረድዋን ሸረፉ ፣ ቤንጃሚን ኮቴ ፣ መድሃኔ ብርሀኔ እና ሐብታሙ ተከስተ የጨዋታ እገዳ ተጣለባቸው

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

 ወላይታ ድቻን  ለማሰልጠን ሁለት አመታትን ለመቀጠል ፊርማውን ያኖረው አሰልጣኝ መሣይ ተፈሪ ከሀትሪክ ጋዜጣ ጋር ያደረገውን ቆይታ እንሇ !!!

Mussie Girmay By Mussie Girmay 9 years ago
ኢትዮጵያ ቡና አጥቂ አስፈረመ
የጨዋታ ዳሰሳ |አርባምንጭ ከተማ ከ ደደቢት
የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ሀገራት ከ23 ዓመት በታች ውድድር አዘጋጅ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡
የጨዋታ ሪፖርት | ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኝው አርባምንጭ ከተማ ኢትዮጲያ ቡናን በማሸነፍ ወሳኝ 3 ነጥብ ማስመዝገብ ችሏል፡፡
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?