የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ረድዋን ሸረፉ (አዳማ ከተማ) ክለቡ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ባደረገው የ21ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 57 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

- ማሰታውቂያ -
2. ቤንጃሚን ኮቴ (መቐለ 70 እንደርታ) ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
ተጋጣሚዎቸ
- ሀዋሳ ከተማ – መቐለ 70 እንደርታ
- ስሁል ሽሬ – መቐለ 70 እንደርታ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ- መቐለ 70 እንደርታ
- መቐለ 70 እንደርታ -ወላይታ ድቻ
- መቐለ 70 እንደርታ – ሐዋሳ ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
3. መድሃኔ ብርሀኔ (መቐለ 70 እንደርታ) በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
ተጋጣሚዎቸ
- መቐለ 70 እንደርታ-መቻል
- ስሁል ሽረ-መቐለ 70 እንደርታ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – መቐለ 70 እንደርታ
- መቐለ 70 እንደርታ – ሐዋሳ ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
4. ሐብታሙ ተከስተ (ፋሲል ከነማ) ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
ተጋጣሚዎቸ
- ፋሲል ከነማ – ሃዋሳ ከተማ
- ሀዲያ ሆሳዕና – ፋሲል ከነማ
- ድሬደዋ ከተማ – ፋሲል ከነማ
- ባህርዳር ከተማ – ፋሲል ከነማ
- ፋሲል ከነማ – ባህርዳር ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።


