ሎዛ አበራ ተቀይራ በገባችበት ጨዋታ ሁለት እጅግ አስደናቂ የሆኑ ግቦችን በማስቆጠር ክለቧ ዲሲ ፓወርን አሸናፊ አድርጋለች።
ዲሲ ፓወር ዳላስ ትሪኒቲን ገጥሞ 3 ለ 2 በረታበት ጨዋታ ላይ በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይራ የገባችው ሎዛ አበራ ሁለት ግቦችን አስቆጥራለች።
ዲሲ ፓወር ሎዛ ከመግባቷ በፊት 2 ለ 0 እየተመራ የነበረ ቢሆንም በ54ኛው እና በ95ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረቻቸው ግቦች ቡድኗን ባለ ድል አድርጋለች።



