የሉሲዎቹ አምበል እና የዲሲ ፓወር አጥቂ የሆነችው ሎዛ አበራ ለክለቧ የመጀመሪያ ጎሏን አስቆጥራለች።
ክለቧ ዲሲ ፓወር ሌክሲንግተንን ባስተናገደበት የምሽቱ ጨዋታ 77ኛው ደቂቃ ላይ ዩካ ኩሮሳኪን ቀይራ የገባቸው ሎዛ በ85ኛ ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥራለች።
ምንም እንኳን በጨዋታው ዲሲ ፓወር 2 ለ 1 ቢሸነፍም ሎዛ አበራ ታሪክ የፃፈችበት ጨዋታ ሆኖ አልፏል።
ሎዛ ዲሲ ፓወርን ከመቀላቀሏ በፊት በቨርጂንያ ማራውደርስ 11 ጨዋታዎች አድርጋ 10 ግብ በማስቆጠር 7 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችታ ማቀበሏ ይታወሳል።
- ማሰታውቂያ -



