” በሚቀጥሉት አመታት በሚኖሩን ስምምነቶች ዲኤስቲቪን ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መጠየቃችን አይቀርም ”
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አ.ማ ዋና ፀሀፊ አቶ ክፍሌ ሰይፈ” Super sportን የሚያክል የስፖርት ቻናል የለም። ” አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ
የSuper sport ልዩ የመክፈቻ እና የአቦል ቲቪ አንደኛ አመት ክብረ በዓል በዛሬው ዕለት ትልልቅ ለመንግሥት ባለስልጣናት የኪነጥበብ ሰዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት አመሻሽ ላይ በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ አስቀድመዉ ንግግር ማድረግ የቻሉት አቶ መታሰቢያ በላይነህ የመልቲ ቾይስ ኢትዮጵያ አባል አጠቃላይ በእስካሁኑ የአንድ አመት የአቦል ቲሌቪዥን ጉዞ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ገለፃን አድርገዋል። ካነሷቸዉ ነጥቦች መካከልም :-
* በአጠቃላይ እስከአሁን በዲኤስቲቪ የተላለፉትን ፕሮግራሞች በዉጭ ሀገር ቋንቋዎች ተተርጉመዉ ለተለያዩ የአለም ክፍሎች ለማሰራጨት ዕቅድ እንደተያዘ ፤
* ዉድድር የሚደረግባቸው ከተሞችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት እንደተሞከረ ፤
* ሁሉንም ባለሙያዎች በሀገር ዉስጥ ሰዎች የመተካት እና የዕዉቀት ሽግግር እየተደረገ ስለመሆኑ እና ተያያዥ ጉዳዮች አንስተዋል።
አቶ ክፍሌ ሰይፈ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ዋና ፀሀፊ በበኩላቸው :-
ለአቦልም ለSuper sport ልዩ ቻናላም እዚህ መድረስ ወይም በዲኤስቲቪ መተላለፍ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በር ከፍቷል ብለን እናስባለን።
ሊጋችን ወደ ዲኤስቲቪ ሲገባ እጅግ ዘርፈ ብዙ ለዉጥ አስመዝግበናል። ከሀብት ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም ዋንጫ የበላ ቡድን 350 ሺ ብር ነበር አሁን ግን ወደ 13 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ያገኛል። ይህ እጅግ አስደናቂ ለዉጥ ነዉ።
ዕቅዳችን በሚቀጥሉት አመታት ከዲኤስቲቪ ጋር ተጨማሪ አመታትን ስንስማማ የተሻለ ገንዘብ ወደ 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ለመጠየቅ ነዉ ነገር ግን ስታንዳርዳችንን እጅግ ማሳደግ አለብን። ሁሉ ነገራችንን አሻሽለን አስተካክለን ከተገኘን የተሻለ ገቢ የማናገኝበት ምክንያት የለም ሲሉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም በዚህ ሂደት ከቀጠልን እግርኳሳችን ከመንግስት ተከሻ ላይ ወርዶ ራሱን የሚችልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። ያሉ ሲሆን በእስካሁኑ ጉዟችን እግጅ ትልቁ የእግርኳሳችን ችገር የመጫወቻ ሜዳ ነዉ። በማለት ንግግራቸዉን አገባደዋል።
በፕሮግራሙ ላይ በክብር ዕንግድነት የተገኘዉ አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ ንግግር ያደረገም ሲሆን በንግግሩ ላይም ዲኤስቲቪ ወደ ሀገራችን በመምጣቱ እጅግ ደስተኛ እንደሆነ እና በፕሮግራሙ ላይ በመታደሙም ክብር እንደተሰማው የገለፀ ሲሆን በምሽቱ ፕሮግራም ላይ ለተገኙት ክቡር ሚኒስተሩም የሀገራችንን የስታዲየም ጉዳይ አፅንኦት ሰጥተዉ እንዲያስቡበት አሳስቧል። የእገርኳ ሜዳዎቻችን የተሰሩት ለሌላ አላማ ይመስላል እንዴት ብሔራዊ ቡድናችን ደቡብ አፍሪካ ሄደው እንዲጫወቱ ይሆናል ሲል ቁጭቱንም ገልጿል።
በነገራችን ላይ ሱፐር ስፖርትን የሚያክል የስፖርት ቻናል የለም ይህንን ደረቴን ነፍቼ እናገራለው ፣ ይህንን እድል መጠቀም ያስፈልጋል ያለ ሰሆን ከዚህ በተጨማሪም በዲኤስቲቪ የእግርኳስ ቀጥታ ስርጭት አስተላላፊ ለሆኑት ጋዜጠኞች ተልቅ ክብር እንዳለዉ ገልፆ ንግግሩን ቋጭቷል።
በዝግጅቱ ላይ የታደሙ ትልልቅ የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች አጫጭር ንግግሮችን አድርገው ዝግጅቱ ተጠናቋል።
አስተያየት ይስጡ