መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ከራይድ ትራንስፖርት ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ሊፈፅም ነዉ !!
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢትዮጵያ ቡና ከራይድ ትራንስፖርት ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ሊፈፅም ነዉ !!

አጋራ
አጋራ

ከወትሮው በተለየ መልኩ ክለቦች ከመንግስት ጥገኝነት ተላቀዉ ራሳቸዉን ለመቻል በሚመስል መልኩ የተለያዩ ስፖንሰሮችን ለማግኘት በሚታትሩበት በዚህ ወቅት የመዲናዋ ክለብ የሆነዉ ኢትዮጵያ ቡና ተጨማሪ ሌላ ስፖንሰር ማግኘቱ ተሰምቷል።

በተለይ ከተለያዩ ስፖንሰሮች ጋር በአጋርነት በመስራት ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች በቀጣዩ ሳምንት ረብዑ ደግሞ ስድስተኛ ስፖንሰሩ ከሚሆነው የራይድ ትራንስፖርት ጋር ረፋድ 3:30 ሰዓት ላይ በሸራተን አዲስ ሆቴል ስምምነቱን የሚፈፅም ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም በዕለተ ማክሰኞ ኢትዮጵያ ቡና ከነባር አጋሩ ከሀ እስከ ፖ ጋር አስቀድሞ ባለዉ ዉል መሰረት የተዘጋጁለትን አዳዲስ ማልያዎቸን እንደሚያስተዋዉቁ ተገልጿል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ እስከዛሬ ከተለያዩ ስፖንሰሮች ጋር በመስራት ላይ ካሉት ኢትዮጵያ ቡና ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ከመሳሰሉት ቡድኖች በተጨማሪም ከቀናት በፊት አዳማ ከተማ ከዋሊን ቢራ ጋር ወደ ስልሳ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብ እና የአይነት ገቢ የማያስገኝለት የአምስት አመት ስምምነት መፈፀሙ ይታወቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...