ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ጥፋተኛ ናቸው ያላቸውና ከፍተኛ ቅጣት ያስተላለፈባቸውን ዳኞች ቅጣት ማቅለሉን አስታውቋል።
በአዳማ እየተካሄደ ባለው የታዛቢዎችና ኮሚሽነሮች የምክክር መድረክ ላይ እንደተገለጸው ኮሚቴውና የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ጠንካራ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ስድስት ወር ተቀጥተው ሶስት ወር ያለፋቸው በምህረት እንዲመለሱ ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲወርድ የተወሰነበት ዳኛ ሁለቴ መቀጣት የለበትም በሚል ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲወርድ የሚለው ውሳኔ መነሳቱን የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ም/ል ሰብሳቢ አቶ ልዑልሰገድ በጋሻው ተናግረዋል።
ኮሚቴው ዳኞችን የማብቃት ስራ ላይ የመስራት እንጂ ዳኞችን የማጥፋት አላማ የለውም ያሉት አቶ ልዑልሰገድ ” እኛ አጥፍተዋል አወዛጋቢ ሪፖርት አቅርበዋል በሚል የቀጣናቸው አንድ ኮሚሽነርና ስድስት ዳኞችን ነው ሊግ ኩባንያው ግን የሚፈልገው ሀያና ሠላሳ ዳኞችን እንድንቀጣ ነው ይሄን አላደረግንም ” ሲሉ አሰሰረድተዋል።
የብሄራዊ ዳኞች ምክትል ሰብሳቢ ልዑል ሰገድ በጋሻው ከዳኝነት ምደባ ጋር ለተያያዘ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “ሁሉንም ዳኞች ማስደሰት አይቻልም በኮታ መስጠትም አይቻልም ክለቦችም ጥያቄ እያቀረቡ በብቃት ይሁን እያሉ ነው ካፍ በአፍሪካ ደረጃ ሁሉንም ማስደሰት ስለማይችል በሀገር ደረጃ ኢንተርናሽናል ዳኞች ሰባት ሰባት ዳኛ ብቻ በኮታ እንዲሆን አድርጎታል። በእኛ ሀገርም 30 የመሃል 50 ረዳት ዳኞች ብቻ ናቸው ፕሪሚየር ሊጉን ማጫወት ያለባቸው ..አሁን ግን 120 ደርሷል እነኚህን ሁሉ ማስተናገድ አይቻልም
ከሴቶች ጋር ተያይዞ የወንድን ፕሪሚየር ሊግ ለማጫወት ሊዲያ ብቻ ለምን ታጫውታለች ለሚለው የፕሪሚየር ሊጉን ፊዚካል ፊትነስን መመዘኛ ማለፍ አለባችሁ ይሄ ከሆነ ችግር የለም ዋናው መመዘኛውን ማሟላት የግድ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
አስተያየት ይስጡ