“ወራጅ ክለቦች አሉ ወራጆቹ ከከፍተኛ ሊግ ሶስት ሁለተኞች ጋር የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አድርገው ሀላፊዎቹ ይታወቃሉ” የሊግ ካምፓኒ አመራሮች

“ፕሪሚየር ሊጉን ላሽነፈ ክለብ
1 ሚሊዮን ብር ይሽለማል”

“ወራጅ ክለቦች አሉ ወራጆቹ ከከፍተኛ ሊግ ሶስት ሁለተኞች ጋር የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አድርገው ሀላፊዎቹ ይታወቃሉ”
የሊግ ካምፓኒ አመራሮች

ሊግ ካምፓኒ በሰጠው መግለጫ ዋንጫውን የሚወስድ ክለብ ሲረጋገጥ ወዲያው ዋንጫው ይሰጣል መርሃ ግብሩ እስኪያልቅ ድረስ አይጠበቅም ዋንጫ ለወሰደ 1 ሚሊዮን ሁለተኛ ለወጣው 700ሺ ሶስተኛ ለወጣው 500ሺ ብር ይሰጣል ተብሏል።

ስለ ዋንጫው የተጠየቁት አመራሮቹ ሲመልሱ ዋንጫው ደቡብ አፍሪካ እየተሰራ ሲሆን ቁመቱ 80ሴ.ሜ ክክብደቱ ደግሞ ከ15-20 ኪሎ ይደርሳል ማንም ኢትዮዽያዊ በዲዛይኑ ላይ መሳተፍ ባለመፍቀዱ ዲዛይኑ ከሀገር ውጪ ሊሰራ መገደዱን አስረድተዋል።

ወራጅ ክለቦች አሉ ወይስ ምን ታስቧል የተባሉት መቶ አለቃ ፈቃደ ማመሞ “ሶስቱ ወራጅ ክለቦች የግድ ይወርዳሉ ከታች ያደጉት ሶስቱ ይመጣሉ። አንድ የትግራይ ክልል ክለብ ቢመጣ ሶስቱ ወራጆች ከከፍተኛ ሊግ ሶስት ምድቦች ሁለተኞች ጋር የጥሎማለፍ ግጥሚያ አደርገው ለሁለቱ ቦታ ይወዳደራሉ”ሲሉ መልሰዋል።

የ2014 መርሃ ግብር በተመለከተ አመራሮቹ እንደገለጹት “ከሀምሌ 1-15/2013 ድረስ ክለቦች ይመዘገባሉ፣ከሀምሌ 1-መስከረም 6/2014 ድረስ የዝውውር መስኮት ይካሄዳል። መስከረም 7/2014 ደግሞ የ2014 የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ ይጀመራል” በማለት እቅድ መያዙን አስረድተዋል።

ኮቪዱ ቢቀጥል በኛ መመዘኛና በክለብ ላይሰንሲንግ መመርያ መሰረት የሚቀጥል ሲሆን በቂ የልምምድ ሜዳና በቂ ሆቴል አለን የሚሉ ከተሞች መወዳደርና ያስተናጋጅ እድል ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል። ምናልባት ህዝብ እንዲገባ ቢፈቀድ በተመረጡና አስተማማኝ ሜዳዎች እንጂ በሁሉም ሜዳዎች አይፈቀድም ሲሉ አሳስበዋል። ከትግራይ ክለቦች መሃል ወልዋሎ አዲግራት ያለፈውን ገንዘብ ላኩልን የሚል ደብዳቤ ከመላክ ውጪ ሌላ ግንኙነት የለንም ሲሉ ተናግረዋል።

“ኮከብ ተጨዋች ምርጫ የሚካሄደው 60 በመቶ
በአሰልጣኝ 40 በመቶ ከህዝብ ድምጽ ይሆናል። ዋንጫውን ሶስት ጊዜ በተከታታይ አንድ ክለብ ቢወስድም ዋንጫውን ማስቀረት አይቻልም። ቅዱስ ጊዮርጊስ በ10 ስፖንሰሮች ቢደገፍም ጨዋታ ሲኖር ስፖንሰሮቹ በስታዲየም አርማቸውን ስታዲየም ውስጥ መጠቀም ላይ ፍቃደኝነቱ ያለ አይመስልም አነጋግረናቸውም ያገኘነው ምላሽ ደካማ ነው። የወልዲያ ስታዲየምን የፊፋ ሰዎች አይተውት ቢደሰቱም በሆቴሉ ግን ደስተኞች አይደሉም ይህን ማስተካከል የግድ ይሆናል ኮቪዱ ባይኖርና ተዟዙሮ ውድድር ቢቀጥል ግጥሚያዎቹ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ግን በተመረጡና ደረጃውን በጠበቀ ስታዲየም ብቻ እንደሚካሄድ ” አስረድተዋል

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport