መነሻ ገጽ ሴካፋ “እንደ ሴካፋ አዘጋጅነታችን ጥሩ ተጫውተን ዋንጫውን ለማንሳት ተዘጋጅተናል”ሀይሌ ገ/ትንሳኤ
ሴካፋቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

“እንደ ሴካፋ አዘጋጅነታችን ጥሩ ተጫውተን ዋንጫውን ለማንሳት ተዘጋጅተናል”ሀይሌ ገ/ትንሳኤ

አጋራ
አጋራ

“ውሌን ገና አልጨረስኩም፤ አሁንም ከቡና ጋር ነኝ፤ ከቡድኑ ጋር የሚኖረኝ ትስስርም እድሜ ልኬንም ይመስለኛል፤ የቡናን ማሊያ አድርጌም የኳስ ጊዜዬን ባጠናቅቅም በጣም ደስ ይለኛል”፡፡

“እንደ ሴካፋ አዘጋጅነታችን ጥሩ ተጫውተን ዋንጫውን ለማንሳት ተዘጋጅተናል”

ሀይሌ ገ/ትንሳኤ


አገራችን ኢትዮጵያ ከሳምንታት በኋላ ለምታስተናግደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ቡድናችን ዝግጅቱን ጀምሮ የውድድሩን መጀመሪያ ቀናት እየተጠበበቀ ይገኛል፤ ዋልያዎቹ ለኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ለሆናቸው የብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች መርጦ እያለማመዳቸው ከሚገኙት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ቡናው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀይሌ ገ/ትንሳሄ ለእዚህ ቡድን ለመመረጥ መቻሉ መደሰቱን ገልፆ ቡድኑ በውድድሩ ቆይታው ሻምፒዮና ለመሆንና የሀገሪቱንም ባንዲራ ከፍ ብሎ ለማስወልበልም መዘጋጀቱን ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ መሸሻ ወልዴ ጋር ባደረገው ቆይታ ሊገልፅ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች የሆነውን ሀይሌን በልምምዳቸው ዙሪያ ከራሱ ጋር በተያያዙ ጉዳዮችና በቤትኪንጉ ክለቡ ቡና ስላሳለፈው ቆይታ አጠር ባለ መልኩ አናግረነው የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቶናል፡፡

ለምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ እያደረጉት ስላለው ዝግጅት

“እስካሁን ጥሩና አሪፍ ልምምድን ነው በአሰልጣኞቻችን አማካኝነት እየተሰጠን በመስራት ላይ የምንገኘው፤ ስራዎቻችንም ከኳስ ጋር የተገናኙና እኛም በጣም የምንወደው አይነትም ነው፤ ደስ ብሎንም በመለማመድ ላይም ነው ያለነው”፡፡

ለብሔራዊ ቡድን የመመረጥ እድሉን ስለማግኘቱ

“ከዚህ በፊት 2010 ላይ በኢትዮጵያ ቡና ተጨዋችነቴ በአሰልጣኝ ዲዲየር ጎሜዝ በምንሰለጥንበት ሰዓትና በምርጥ ብቃት ላይም በተገኘሁበት ሁኔታ ከ20 ዓመት በታች ላለው የወጣት ብሔራዊ ቡድን የመመረጥ እድሉን አግኝቼ ምክንያቱን ፈፅሞ ባላወቅኩበት ሁኔታ ተዘልዬ ነበር፤ ያኔ ቆጭቶኝ ነበር፤ ዘንድሮ ደግሞ በኢትዮጵያ ቡና አዲስ የአጨዋወት እንቅስቃሴ ውስጥ ጥሩ ብቃቴን ላሳይ ስለቻልኩ ዕድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ለሆነው የብሔራዊ ቡድን ልመረጥ ስለቻልኩ በጣም ነው የተደሰትኩት፤ በዚህ ቡድን ቆይታዬም ጥሩ ነገሮችን ሰርቼም የዋናውን ቡድን ለመቀላቀልና ከዋልያዎቹም ጋር ደማቅ ታሪክን ለሀገሬ ለማስፃፍም ከፍተኛ ጥረትንም አደርጋለው”፡፡

ስለ ብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ

“ጥሩ ጥሩ ልጆች በስኳዱ ውስጥ አሉ፤ ጥሩ አሰልጣኞቹም አሉን፤ ከሱፐር ሊግ አንስቶ እስከ ፕሪምየር ሊግ ደረጃም ያሉ ተጨዋቾችንም በማካተትም ነው ቡድኑ የተገነባውና አሪፍ ነገርን በሜዳ ላይ ልናስመለክት ተዘጋጅተናል”፡፡

በውድድሩ ተሳትፎ ሊያመጡ ስላሰቡት ውጤት

“የሴካፋ አዘጋጅ ነን፤ ዋንኛው ታርጌታችን ውጤት ማምጣት ነው፤ የውድድሩ ሻምፒዮና መሆንን በጣም እንፈልጋለን፤ ይሄን ውጤት ማምጣት የምንፈልገው ደግሞ ጥሩ እግር ኳስንም ለተመልካቹ በማሳየት ጭምር ነው”፡፡

ለሀይሌ የውድድር ዘመኑ ምርጥ ነበር?

“አዎን፤ ከክለቤ ቡና ጋር ጥሩ የውድድር ዘመንን አሳልፌ ክለቤን ከጓደኞቼ ጋር በመሆን ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ለማሳለፍ ችያለው፤ ጥሩ የውድድር ዘመንን ባሳለፍኩበት በዚሁ ጊዜም ለብሔራዊ ቡድንም ለመመረጥም ችያለውና ይሄ ለእኔ አስደሳቹ ነገር ነው”፡፡

ኢትዮጵያ ቡናን በኮንፌዴሬሽን ካፑ በምን መልኩ እንጠብቀው?

“ይሄ ተሳትፎ ለክለቡ የተገኘው ከ9 ዓመታት በኋላ ነው፤ ከዚያ በፊት በነበረው የቡድኑ የኢንተርናሽናል የውድድር ተሳትፎ ጉዞ ደግሞ እስከ 16 ቡድኖች እስከሚገኙበት ደረጃ ላይ ነበርና በዚህ የአፍሪካ ክለቦች የውድድር ተሳትፎአችን ምርጡን ቡናን ከጥሩ የእግር ኳስ ጨዋታው ጋር በማቅረብ ይህን የውጤት ሪከርድን ለመስበርም ጭምር ነው የምንዘጋጀው”፡፡

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ስለሚኖረው ቆይታ

“ውሌን ገና አልጨረስኩም፤ አሁንም ከቡና ጋር ነኝ፤ ከቡድኑ ጋር የሚኖረኝ ትስስርም እድሜ ልኬንም ይመስለኛል፤ የቡናን ማሊያ አድርጌም የኳስ ጊዜዬን ባጠናቅቅም በጣም ደስ ይለኛል”፡፡

ስለ ፋሲል ከነማ ሻምፒዮናነትና ስለ አቡበከር ናስር ኮከብነት

“ፋሲሎች ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን ባለፉት ሶስት ዓመታትም ብዙ ለፍተዋል፤ ጥሩ ተጨዋችና አሰልጣኞች አላቸው፤ ውጤቱም የሚገባቸው ነው፤ ስለ አቡኪ ማለት የምፈልገው ደግሞ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ከዚህ በላይም ክብርና ሙገሳ ይገባዋል”፡፡

ስለ ቀጣይ ጊዜ እልሙ

“የማንኛውም ስፖርተኛ ግብና እልም በእግር ኳሱ ለታላቅ ደረጃ መብቃት ነው፤ እኔ አሁን ያን ለማሳካት ጥረትን ጀምሬያለው፤ ሰው ያስባል፤ ፈጣሪ ደግሞ ይፈፅማልና ራሴን በተሻለ መንገድ በማቅረብ ስኬታማ ጊዜያቶችን እንደ ቡድንም እንደ ግልም ለማግኘት እያለምኩኝ ነው”፡፡

በመጨረሻ

“በኢትዮጵያ ቡና የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ ለብሄራዊ ቡድን ለመመረጥ በመቻሌ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ለሀገሬ ጥሩ ነገር የመስራት ከፍተኛ ራዕይ አለኝ፤ ይሄን በቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወቴ በቀዳሚነት የማስበውም ነገር ነው፤ ሌላው ከቡናም ጋር የሊግ ዋንጫን የማንሳት ትልቅ ሀላፊነትም በቀጣይ የውድድር ዘመን ይጠብቀኛልና ስለዛም እያሰብኩ ነው፤ ይህን ካልኩ ሌላ ልጨምር የምፈልገው ሀሳብ የቡና ደጋፊዎች የክለቡ የልብ ደጋፊዎችም ናቸውና ከክልል ወደ ክልል እየተጓዙ ለሚያደርጉልን ድጋፍ ከልብ ላመሰግናቸው እፈልጋለው፤ አሰልጣኞቻችን የቡድናችን አመራሮችና የቡድናችንም ተጨዋቾች የምስጋናው ተቋዳሽ እንዲሆኑም እፈልጋለው”፡፡

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...