የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዜዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ እንዳሉት ከሰኔ 26 ጀምሮ ሊደረግ መርሐግብር ወጥቶለት የነበረዉ ውድድር ሀምሌ 10 እንደሚጀምር ዘሬ እየሰጡት በሚገኘዉ መግለጫ ገልፀዋል።
ለዉድድሩ መራዘም እንደምክንያትነት የተቀመጠዉም ካፍ ለሴካፋ የሚለቀዉ በጀት ከሀምሌ 1 ጀምሮ ስለሆነ እና በሻምፒዮናው ላይ የምትካፈለዉ ደቡብ ሱዳን በአረብ ሊግ ላይ እየተሳተፈች ስለምትገኝ ነዉ።