ለካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ዶክተሩ አርቢትር ተመደበ

 

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ከ10 ቀን በኋላ ኪጋሊ ላይ የሚደረገውን የሩዋንዳው ስፖርቲቭ ኪጋሊና የቦትስዋናው ኦራፓ ዩናይትድ ጨዋታን አራት ኢትዮጲያዊያን አርቢትሮች እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡

የጨዋታው የመሃል ዳኛ ሆኖ የተመረጠው ኢትዮጲያዊው ኢንተርናሽናል አርቢትር ዶክተር ሃ/የሱስ ባዘዘው ሲሆን ረዳቶቹ ደግሞ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ሸዋንግዛው ተባባልና ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴ መሆናቸው ታውቋል፡፡ አራተኛ ዳኛ ኢንተርናሽናል አርቢትር አማኑኤል ሃይለስላሴ ሲሆን ኮሚሽነሩ ቡሩንዳዊው ሙስጠፋ ሳሙጋቦ መሆናቸው የወጣው መረጃ ያስረዳል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport