ኤርነስት ሚደንዶርፕ ወደ ሌላ ክለብ ሊያመሩ ይሆን ?
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መለያየታቸው የተገለፀው ኤርነስት ሚደን ዶርፕ የሁለት ወር ደሞዝ በካሳ መልክ እንዲከፍሉ ሲገደዱ ከ ደቡብ አፍሪካው ማሪትዝበርግ ክለብ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቸው ተገልጿል ።
ማሪትዝበርግ ክለብ በደቡብ አፍሪካ ሊግ ያሳየውን ደካም ጅማሮ ተከትሎ በትላንትናው ዕለት ዋና አሰልጣኙን ማሰናበቱ ሲታወቅ ከዚህ ቀደም በሶስት የተለያዩ አጋጣሚዎች ክለባቸውን ያሰለጠኑትን ሚደንዶርፕ ለመቅጠር ታውቋል ።
የማሪትዘበርግ ክለብ አመራሮች እንዳሳወቁት ሚደንዶርፕ ቅድሚያ የተሰጣቸው አሰልጣኝ መሆናቸውን እና የሀገሪቱን እግር ኳስ ባህል ጠንቅቀው መረዳታቸው ዳግም ፊታቸውን እንዲያዞሩባቸው እንዳደረጋቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል ። ይህንንም ተከትሎ ከመጪው አርብ በፊት ማሪትዝበርግ አዲሱን አሰልጣኛቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ በመረጃው ተገልጿል ።
ማሪትዘበርግ ክለብ በመጪው አርብ በሊጉ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ጋር ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የወጣው መርሀ ግብር ያሳያል ።