የላይቤሪያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰላም ዘርዓይ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ሴት ታራሚዎች የአሰልጣኝነት ስልጠና ሰጥታለች።
ስልጠናው የካፍ ዲ ላይሰንስ ሲሆን በላይቤሪያ ሞንሮቪያ ማዕከላዊ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ 19 ሴት ታራሚዎች የተሰጠ ነው።
የስምንት ቀናት ቆይታ የነበረው ስልጠናው በኢንስራክተር ሰላም ዘርዓይ እና በቀድሞው የላይቤሪያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮበርት ላርቴይ የተሰጠ ሲሆን ከላይቤሪያ እግር ኳስ ማህበር ምስጋና ተችሯቸዋል።
ኢንስራክተር ሰላም ስልጠናውን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጿ ባሰፈረችው መልዕክት ዛሬ ምንም ቢፈጠር ወይም የቱንም ያህል መጥፎ ቢመስልም ህይወት ትቀጥላለች ነገም የተሻለ እንደምትሆን ከስልጠናው ትምህርት ወስጃለሁ ብላለች።
- ማሰታውቂያ -

በተጨማሪም ለካፍ እና ላይቤሪያ እግር ኳስ ማህበር የሴቶች ዲፓርትመንት እንዲሁም ሚስተር ካንየን እና ኢንስራክተር ሮበርት ምስጋናዋን አቅርባለች።



