የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የድሬዳዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ በፕሪሚየር ሊጉ ወድድር አመራርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ የዘጠኝ ጨዋታ ዕግድ ተላልፎባቸዋል።
አሰልጣኙ ዕግዱ ሊተላለፍባቸው የቻለው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በነበረው ጨዋታ ላይ የዕለቱን ዋና ዳኛ አፀያፊ ስድብ ተሳድበው በ44ኛ ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ በመሰናበታቸው ነው ተብሏል።
በተጨማሪም በዕረፍት ሰዓትም በመልበሻ ክፍል አካባቢ ዋና ዳኛውን በድጋሚ አፀያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ይፋ የሆነው የቅጣት ሪፖርት አመላክቷል።
ስለሆነም አሰልጣኙ ቀይ ካርድ ለተመለክቱበት ሶስት ጨዋታዎች እንዲታገዱና አስር ሺህ ብር እንዲከፍሉ እንዲሁም አጸያፊ ስድብ ለተሳደቡበት ስድስት ጨዋታዎች እንዲታገዱና አምስት ሺህ ብር እንዲከፍሉ በድምሩ ዘጠኝ ጨዋታዎች እንዲታግዱና አስራ አምስት ሺህ ብር እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።
- ማሰታውቂያ -

አሰልጣኝ ይታገሱ በቅጣቱ ምክንያት ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ድቻ ጋር እስከሚያደርገው የውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ ድረስ ቡድናቸውን የማይመሩ ይሆናል።


