አዲስ የተቀጠሩት እና ዛሬ ቡድኑን የመሩት አሰልጣኝ መሳይ በየነ ቡድኑን በአንድ ጨዋታ ከወራጅ አውጥተውታል።

ሐረር ከተማን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ምድብ ሀ በሊጉ እንዲያቆዩ ተቀጥረው በሁለተኛው ዙር አምስት ጨዋታዎች የመሩት ሐረር ከተማዎች አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው (ማንጎን) በማሰናበት በምትኩም የቀድሞው የቡታጂራ እና ቡራዩ ከተማ አሰልጣኝ የሆኑት መሳይ በየነ ተረክበዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ፣ ባህርዳር ከተማ ፣ ሀድያ ሆሳዕና ፣ ጅማ አባጅፋር እና አዲስ አበባ ከተማ አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ጳውሎስ ክለቡን ለማትረፍ በሁለተኛው ዙር እስማኤል አቡበከርን ተክተው ቡድኑን ቢረከቡም በውጤት መጥፋት እና በሌሎች ሚስጥር ናቸው በተባልኩት ጉዳዮች ተካተውበት ከአሰልጣኝነት ተሰናብተዋል።
ዛሬ ቡድኑን የተረከቡት አሰልጣኝ መሳይ በየነ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ነቀምት ከተማን 3ለ1 በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠናው ግርጌ በመውጣት በ10 ነጥቦች 8 ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለ ሲሆን በምትኩ አቃቂ ቃሊቲ ወደ ወራጅ ገብቷል።
አስተያየት ይስጡ