ነገ በድሬዳዋ ስታዲየም ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደጋፊው ፊት ጨዋታ ሊያደርግ ነው።

በአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሁለት ቀን በፊት ቅዳሜ ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ከሜዳው ውጪ ሞሮኮ ላይ ሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔን የረቱት ዋልያዎቹ የመልስ መርሀግብራቸውን ከአመታቶች በኋላ በድሬዳዋ ስታዲየም ላይ ነገ አስር ሰዓት ላይ ያከናውናሉ። ለዚህ ጨዋታ ብቻ ፍቃድን ያገኘው የድሬዳዋ ስታዲየም በካፍ በመጣ መመሪያ ያለ ደጋፊ በዝግ እንዲደረግ ቀደም ተብሎ መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ባደረግነው ጥልቅ የመረጃ ማሰባሰብ የነገው ጨዋታ ደጋፊዎች ገብተው እንዲታሙ እና ሀገራቸውን እንዲደግፍ ለማድረግ በጥረት ላይ መሆኑን ባገኘሁት መረጃ ለማረጋገጥ የቻልኩ ሲሆን ነገ ደጋፊዎች ገብቶ ሀገሩን እንደሚመለከት ይጠበቃል።
ይህ ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ስራ አስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን እና ሌሎች የፌድሬሽኑ አመራሮች ሚና ከፍ ያለ መሆኑንም ማረጋገጥ ችለናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከነገው ጨዋታ በፊት አመሻሹን የመጨረሻ ልምምዱንም ሰርቶ ከደቂቃዎች በፊት አጠናቋል።
አስተያየት ይስጡ