አንድሪውስ ኦውሱ በሀድያ ሆሳዕና ውሉን አራዝሟል።

በሆሳዕና ከተማ ለ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዲሱ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ እና ረዳቶቻቸው መሪነት የጀመሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች የጋናዊውን ግብ ጠባቂ አንድሪውስ ኦውሱ ውል ለተጨማሪ አንድ አመት አራዝመዋል።
ከሀገሩ ክለብ አክራ ላዮንስ በኋላ በሞልዶቫው ስፓርታኒ የተጫወተው እና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በመምጣት በፕሪምየር ሊጉ ለሀድያ ሆሳዕና በ26 ጨዋታዎች በቋሚነት የተሰለፈው ይህ የግብ ዘብ በክለቡ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን መቆየቱን ዕርግጥ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ