መነሻ ገጽ ዜናዎች ጋሞ ጨንቻ ሦስት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን አስፈረመ
ዜናዎችየዝውውር ዜናዎችጋሞ ጨንቻ

ጋሞ ጨንቻ ሦስት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን አስፈረመ

አጋራ
አጋራ

ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሚካፈሉበት ጋሞ ጨንቻዎች ሦስት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን አስፈረመዋል

በአሳዳጊ አሰልጣኙ ማቲያስ ለማ መሪነት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካፈሉበት የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአርባምንጭ ከተማ የቅድመ ውድድራቸውን የጀመሩት ጋሞ ጨንቻዎች ሦስት አዳዲስ የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ክለቡ ለሀትሪክ ስፖርት በላከው መረጃ አመላክቷል።

የክለቡ የመጀመሪያ የውጪ ዜጋ የናይጄሪያ ዜግነት ያለው የ22 አመት ዕድሜ እንዳለው የተነገረለት ቤሎ ማርቲንስ ነው። ለሀገሩ ክለቦች ሰንሻይን ስታር ፣ አኩዋ ዩናይትድ ፣ ሪሞ ስታርስ ፣ ለግብፁ ሞደርን እና እንዲሁም የተጠናቀቀውን አመት ደግሞ በሀገሩ ክለብ ሪቨር ዩናይትድ ቆይታን ካደረገ በኋላ አዲስ አዳጊዎቹን ተቀላቅሏል።

ሁለተኛው ፈራሚ ማሊያዊው የመሐል ተከላካይ ቤካዬ ሜሪ ዲያኪቴ ሆኗል። 26 አመት እንዳለው የተነገረለት ይህ ተጫዋቹ የእግር ኳስ ህይወቱን ለሴኔጋሉ ጎዲ አዋዬ ለቶጎው አስኮ ካራ ፣ ለሞልዶቫው ሳካሳን ፣ ለኮትዲቫሮቹ ስቴላ እና ኤል ዋይሲ ሳሳንደራ እንዲሁም የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ደግሞ ወደ ሞሪታኒያ በማምራት ቼማል በተባለ ክለብ ቆይታን አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ አምርቷል።

ሦስተኛው ፈራሚ ደግሞ የቻድ እና የካሜሮን ጥምር ዜግነት ያለው ቻዳዊው የ32 አመት ግብ ጠባቂ ጆርዳይን ማባይንአሲም ነው። 1 ሜትር ከዘጠና አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው እና ለካሜሮኖቹ ክለቦች ሬኔሳንስ ፣ ሌስ አስተርስ ፣ ኒው ስታርስ እና ካነን ያሁንዴ ፣ ለካዛኪስታኑ ዜስካ ዱሻንቤ ለጋናው ፓራ ሬንጀርስ የተጠናቀቀውን አመት ለደቡብ አፍሪካው ክለብ ለቬንዳ ከተጫወተ በኋላ ቀጣይ ማረፊያው ጋሞ ጨንቻ መሆኑ ዕርግጥ ሆኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...